Category: News

embassy news

ከኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ ማህበረሰብና የተለያዩ ሚሲዮኖች ለኮሮናቫይረስ መከላከል ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ

በተለያዩ አገሮች ከሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖችና ዳያስፖራ ማህበረሰብ ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ መሰብሰቡን የውጭ አገሮች ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስታወቀ።

ዓለምን ለሁለንተናዊ ቀውስ እየዳረገ ባለው የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ሉላዊ ወረርሽኝ የሚያስከትለውን ጫና ለመቋቋም አገሮች የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።

ኢትዮጵያም በውጭና በአገር ውስጥ ያሉ ዜጎችን የተባበረ ክንድ በመሻት ብሔራዊ የኮሮናቫይረስ መከላከል የሀብት አሰባሳቢ ግብረኃይል በማቋቋም ወደ ስራ ከገባች ሰነባብታለች።

በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያንም የተቻላቸውን እጃቸውን በመዘረጋት ላይ ሲሆኑ በውጭ የሚገኘውን ድጋፍ የሚያሰባስበው የግብረሃይሉ አንዱ ክንፍ ነው።

የውጭ አገራት ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የውጭ ጉዳይ ሚኒስር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ማምሻውን ለኢዜአ በሰጡት መግለጫ፤ ኮሚቴው በየክፍላተ ዓለም ከሚገኙ ሚሲዮኖችና የዳያስፖራ ማህበረሰብ በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ የማሰባሰብ ተግባር ላለፉት 15 ቀናት አከናውኗል።

በዚህም ኮሚቴው በሚሲዮኖች የአደራ ሂሳብ ቁጥር፣ በባንኮች ሬሚታንስ፣ በኢትዮ ቴሌኮም ድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕላትፎርም የተዘጋጁ ሲሆን በዚህም በየአገሮች የሚገኙ 60 ሚሲዮኖች ሰራተኞችና የዳያስፖራ አባላት በገንዘብ፣ በአይነትና በሙያ ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የዳያስፖራ ማህበረሰቡ ከዚህ በፊት በተለያየ አገራዊ የልማት ስራዎችና የአደጋ ጊዜ አለኝታ ሆኖ መቆየቱን የገለጹት አምባሳደር ብርቱካን፤ ”የወቅቱን ድጋፍ ለየት የሚያደርገው ወረርሽኙ ዓለም አቀፋዊ ቢሆንም ዳያስፖራው ከራሱ አልፎ ወገኑን የማስቀደም ተግባር ላይ መሰማራቱ ነው” ብለዋል።

በዚህም እስካሁን በተደረገው እንቅስቃሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞችን ጨምሮ ከ60 ሚሲዮን ሃላፊዎችና ሰራተኞች ከ3 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ ተችሏል።

በተለያዩ አገሮች ከሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በድምሩ 14 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።

ከነዚህም መካከል ከአቡዳቢ 2 ሚሊዮን፣ ከዱባይ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን፣ ከቤጂንግ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን፣ ከካናዳ ኦታዋ 1 ሚሊዮን እንዲሁም ከስዊዘርላንድና ኦስትሪያ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተገኝቷል።

”በዚህም በድምሩ 18 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የተገኘ ሲሆን ሁሉም በኮሚቴው እጅ የገባ ድጋፍ ነው” ብለዋል።

በሌላ በኩል ኢትዮ-ቴሌኮም ባመቻቸው ኢትዮሬሚት የተሰኘ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስርዓት ከ302 ሺህ 587 ብር በላይ እንደተሰበሰበ ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ከዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አባላት በኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር ከ32 ሚሊዮን የሚገመት ድጋፍ ለማሰባሰብ ከሰሞኑ ቃል መግባታቸውን ገልጸዋል።

ኮሚቴው ባይረከብም በዋሽንግተን በኢንተርኔት ገንዘብ ማሰባሰቢያ ስልት ‘ጎፈንድሚ’ አማካኝነት 27 ሚሊዮን ብር የሚገመት ገንዘብ እንደተሰበሰበ መመልከታቸውን ገልጸዋል።

የዳያስፖራ አባላቱ በገንዘብ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የህክምና መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች በአይነት ድጋፍ በሚሲዮኖች በኩል እያደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በዚህም ከፓሪስ፣ ፍራንክፈርት፣ ስዊዘርላንድ፣ ኒው ደልሂ፣ ዱባይ፣ ሎስአንጀለስ፣ ቻይና፣ ጆሀንስበርግ፣ ዋሽንግተን የተለያየ የቁሳቁስ ድጋፍ መገኘቱን ገልጸዋል።

ከድጋፎች መካከልም የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ፣ መድሃኒት፣ የእጅ ጓንት፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል፣ የሙቀት መለኪያ መሳሪያና የሆስፒታል አልጋዎች ይገኙበታል።

እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ ቤታቸውን መንግስት በሽታውን ለመከላከል ለማንኛውም አገልግሎት እንዲጠቀምበት የለገሱ ኢትዮጵያዊያንም መኖራቸው ተገልጿል።

ለአብነትም በፍራንክፈርት ነዋሪ የሆኑት አቶ ብሩክ ወልዴ ዓለምገና ከተማ የሚገኝ ባለ18 መኝታ ክፍል ፔንሲዮን ለግሰዋል።

የሎስአንጀለስ ነዋሪ የሆኑት አቶ ታሪኩ ክፍሌና ባለቤታቸው ወይዘሮ ፍሬህይወት ጥጉ ሰበታ ከተማ የሚገኝ ህንጻ አበርክተዋል።

ጆሃንስበርግ የሚኖሩት አቶ ዳግማዊ መኮንንና ባለቤታቸው ሕይወት አየነው አዲስ አበባ የሚገኝ ሆቴል ሲለግሱ የአብሲኒያ አየር መንገድ ባለቤት አቶ ሰለሞን ግዛው ለአደጋ ጊዜ ነጻ የሄሊኮፕተር በረራ አገልግሎት ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

ለችግር ጊዜ ለወገናቸው ለቆሙ ኢትዮጵያዊያን ምስጋና ያቀረቡት አምባሳደር ብርቱካን፤ በየአገሮቹ ካለው የዳያስፖራ መጠን አንጻር አሁንም ድጋፉን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅቱ ከማንኛውም አመለካከት በላይ መተሳሰብን በተግባር ማረጋገጥ የሚያስፈለግበት በመሆኑ በውጭም በአገር ውስጥም ያሉ ኢትዮጵያዊያን ይህን ክፉ ጊዜ በመተባበር ማለፍ አለብን ሲሉ ጠይቀዋል።

Office of the Prime Minister Gives Clarification Statement on the State of Emergency

Billene Seyoum, from the Press Secretariat Unit of the Prime Minister Office of Ethiopia, today (April 09) gave a short video briefing aiming at providing context and clarity on the declaration of the State of Emergency that was declared by the Council of Ministers yesterday (April 08).

According to Billene, since the announcement yesterday there have been various speculations surrounding the decree which require some clarification.

In her attempt to clarify the major points, she said: “There are a lot of shifting variables and dynamics that the health crisis introduces which cannot be treated and addressed under a blanket state of emergency which is a uniform over time. Therefore, the announcement of a state of emergency yesterday is a decree to prepare the foundation for subsequent binding regulations that will be set by the federal government assessing these various shifting trends and dynamics that the virus will entail.”

According to the statement, the key characteristics of the state of emergency will include
1. The impositions are subject to vary
2. The impositions are binding on all Ethiopians and non-Ethiopians that are dwelling in the country
3. The scope of impositions can change from geographic location to geographic location depending on the severity of the threat
4. The imposition can change over time depending on the threat level assessments
5. The imposition can contract and expand within the five-month duration depending on the consistent threat level assessments that the federal government is undertaking.

The briefing also tries to address some issues that need some clarification including the rationale behind having a 5-month decree. Click here for more: https://bit.ly/3eiiPtM

ADB unveils 10 bn USD response facility to curb COVID-19

The African Development Bank Group unveils 10 billion USD for the creation of COVID-19 Response Facility to assist regional member countries in fighting the pandemic.

In a press release, AfDB revealed that the facility is the latest measure taken by the Bank to respond to the pandemic and will be the institution’s primary channel for its efforts to address the crisis.

President of the AfDB, Akinwumi Adesina said the package took into account the fiscal challenges that many African countries are facing.

“Africa is facing enormous fiscal challenges to respond to the coronavirus pandemic effectively,” he said.

He noted that the AfDB is deploying its full weight of emergency response support to assist Africa at this critical time.

“We must protect lives; this Facility will help African countries to fast-track their efforts to contain the rapid spread of COVID-19,” he added.

The Facility entails 5.5 billion USD for sovereign operations in African Development Bank countries, and 3.1 billion USD for sovereign and regional operations for countries under the African Development Fund, the Bank Group’s concessional arm that caters to fragile countries.

An additional 1.35 billion USD will be devoted to private sector operations, he mentioned.

“These are extraordinary times, and we must take bold and decisive actions to save and protect millions of lives in Africa. We are in a race to save lives. No country will be left behind,” Adesina said.

African Leaders, Including President Sahle-Work, Back WHO

 

Ethiopia’s President Sahle-Work Zewde has joined the chorus of support for WHO Director General, Dr Tedros Adhanom.

“WHO under Dr Tedros effective leadership, are delivering on their mandate at a time we need them most. Let’s give them the space,” she tweeted.

Her remarks came following the US government’s accusation of WHO of being biased in favour of China in response to the coronavirus (COVID-19) pandemic.

“Our global priority is to save lives. COVID-19 is killing many. We must support and protect the most vulnerable. Now is not the time for blame game,” President Sahle-Work said.

Several African leaders also rejected the criticism by the US president on the UN health agency.

The presidents of Rwanda, South Africa, Nigeria and Namibia, along with Chairperson of the African Union Commission and the UN Secretary General rallied in support of WHO.

“Surprised to learn of a campaign by the U.S. government against WHO’s global leadership,” said a tweet by Moussa Faki Mahamat, Chairperson of the African Union Commission.

He said the African Union fully supports the WHO and its Director-General. “The focus should remain on collectively fighting COVID-19 as a united global community. The time for accountability will come.”

Later he added: “I certainly do not imply that it is WHO or Dr. Tedros that need to account in this regard.”

Rwandan President Paul Kagame tweeted that he totally agreed with the African Union leader. He said Dr. Tedros had the “full confidence and support of Africa.” He added: “Save us [from] too much politics, Africa does not need it.”

South African President Cyril Ramaphosa said in a tweet that the WHO is providing “exceptional” and “incalculable” leadership, adding that international solidarity is “the most potent weapon” against the pandemic.

Namibian President Hage Geingob added his support for the WHO and Dr. Tedros. “Global solidarity has become critical,” he said on Twitter. “Let’s hold hands in this crucial moment and focus on what matters, saving lives.”

United Nations Secretary-General Antonio Guterres also expressed his support for the WHO, calling it “absolutely critical” to the war against the coronavirus.

He said the WHO’s response can be debated after the pandemic is over. “Now is not that time. Now is the time for unity.”

Commenting on the accusation by the US government, Dr Tedros said “For us small and big is the same. For us people in the North or in the South, East or West are the same”.

Dr Tedros said he has been targeted with racist attacks and death threats as the agency became embroiled in an increasingly polarized and heated political environment worldwide.

He said the personal attacks on him began more than two months ago. “Abuse, or racist comments, giving me names, black or Negro … even death threats.”

He called for a “quarantine” on divisive political attacks on the novel coronavirus response. “If you don’t want many more body bags, then you refrain from politicizing it,” he said.

He called for global solidarity, warning the world’s countries that they would be “playing with fire” if they try to exploit the pandemic for political purposes.

“If you don’t believe in unity, please prepare for the worst to come.”

Parliament To Hold Extraordinary Session Tomorrow

The House of People’s Representatives of Ethiopia (parliament) will hold an extraordinary meeting tomorrow.

The parliament is expected to approve the state of emergency and its inquiry board members.

The Council of Ministers yesterday declared a five-month state of emergency to avert the spread of coronavirus (COVID-19) and reduce its impact on the country.

The parliament is also expected to approve the loan agreement signed with the International Development Association (IDA) to help Ethiopia’s COVID19 response efforts.

Ethiopia Records One New COVID19 Case

The Ministry of Health has confirmed one new case of coronavirus (COVID19) out of the 294 samples that were tested over the past 24 hours.

This brings the total COVID19 cases in Ethiopia to 56.

The new case is a 43-year-old Ethiopian born Canadian, with a travel history from Canada to Dubai and then to Addis Ababa, according to the Ministry.

Ethiopia has so far registered two deaths and four recoveries from the virus.

Council Of Ministers Holds Urgent Session, Passes Decisions

In its 18th urgent session held on April 8th, the Council of Ministers has passed decisions after deliberating on different issues.

The Council first discussed on the state of emergency draft bill issued to avert the spread of coronavirus (COVID-19) and reduce its impact, according to a statement issued by office of the Prime Minister.

The draft bill was issued in accordance to Article 93 of the Constitution and was needed to respond to the political and socio-economic impact of the pandemic, it said.

Following the declaration of coronavirus a global emergency by the World Health Organization (WHO), about 70 countries have declared state of emergency to halt the spread and protect their people from the virus, it said.

After an in-depth deliberation and with a slight change, the Council of Ministers has decided the draft bill to enter into force as of  April 8, 2020, the statement indicated.

The Council also discussed the draft bill approving three loan agreements signed with the International Development Association (IDA), a financial institution which offers concessional loans and grants to developing countries.

The three agreements are $41.3m loan for Ethiopia’s COVID19 emergency response, $54.9m for the second Africa CDC regional investment project and $134.6m for Ethiopia’s growth and competitiveness programmatic development policy project.

The Council sent both draft bills to be approved by the House of People’s Representatives (parliament).

Ethiopia Declares State Of Emergency Over COVID19

Ethiopia has declared state of emergency in response to coronavirus (COVID19) pandemic.

The move came as the number of COVID19 cases has shown rapid increase in the country, according to a statement issued by the government.

Ethiopia has so far registered 52 confirmed cases, with two deaths and four recoveries.

Despite the various measures taken by the government, data shows a rapid rise in COVID-19 infections, the statement added.

As part of efforts to contain the spread of the virus, schools and universities were closed and non-essential workers told to work from home.

According to the latest figures from Johns Hopkins University, more than 1.4 million cases of coronavirus have been registered globally.

More than 82,000 people have died and more than 300,000 have recovered from the virus.

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ ማወጁን ተከትሎ ያስተላለፉት መልዕክት

ክቡራትና ክቡራን ኢትዮጵያውያን

እየተመለከታችሁትና እየታዘባችሁት እንደሆነው ዓለም በአስቸጋሪ የፈተና ምእራፍ እያለፈች ነው፡፡ ዓለም ይሄንን መሰል ነገር ሲገጥማት ከመቶ ዓመት በኋላ የመጀመሪያ ነገር ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሮና (ኮቪድ -19) የዓለም ሁለንተናዊ ችግር ሆኖ ብቅ ካለበት ጊዜ ጀምሮ ደረጃ በደረጃ የመፍትሔ ርምጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል፡፡ ሕዝቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ፣ የሕክምና ተቋማት እንዲዘጋጁ፣ የመከላከያና የሕክምና መሣሪያዎች ከውጭ እንዲገቡ፣ የማቆያ ሥፍራዎች እንዲዘጋጁ፣ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ፤ አብዛኞቹ የመንግሥት ሠራተኞች በቤት እንዲወሰኑ፣ ብዙ ሕዝብ ሊሰበሰብባቸው የሚችሉ ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ተቋማት አገልግሎታቸውን ሕዝብ ሊሰበሰብ በማይችልበት መንገድ እንዲከውኑ፣ በአብዛኛው ሥፍራዎች የሕዝብ ትራንስፖርት እንዲቋረጥ፣ ለአስቸጋሪ ጊዜ የሚሆን ሀብት የማሰባሰብ ሥራ እንዲሠራ ተደርጓል፡፡

መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝን በተመለከተ የሚከተለው ስትራቴጂ በመከላከል ላይ ያተኮረ ነው፡፡
1. ኅብረተሰቡን አስተባብሮ በባለሞያዎች ምክር መሠረት ለመከላከል መቻል

2. ከመከላከል ያለፈ ነገር ሲመጣ ለማከም የሚያስችሉ ዐቅሞችን ማዳበር፡፡

3. የከፋው ነገር ከመጣም አስቀድሞ በመዘጋጀት እንደየ አስፈላጊነቱ ተገቢ ውሳኔዎችን እያሳለፉ መሄድ፡፡
እስካሁንም በዚህ መንገድ ነው የተጓዝነው፡፡

አሁን ያሉን መረጃዎች እንደሚያሳዩት በቫይረሱ የተያዙ ወገኖች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው፡፡ ይሄም በመሆኑ ሁላችንም ያለንን ዐቅም ሁሉ አስተባብረን ወገኖቻችንን ከዚህ ወረርሽኝ ለመከላከልና የታመሙትንም ለማዳን ማዋል አለብን፡፡ ያለንበት ጊዜ ሕዝብና ሀገርን ለማዳን ሲባል አስቸጋሪ የተባሉ ውሳኔዎችን መወሰን ያለብን ጊዜ ነው፡፡ ይህም ውሳኔ፣ እንደ ግለሰብ፣ እንደ ማኅበረሰብ፣ እንደ ተቋምና እንደ መንግሥት የሚወሰኑ ናቸው፡፡

ይህ ውሳኔ በዛሬው ትውልድ ላይ ብቻ የምንወስነው ውሳኔ አይደለም፡፡ በልጅ ልጆቻችን ላይ ጭምር የምንወስነው ነው፡፡ በዛሬዋ ኢትዮጵያ ላይ የምንወስነው ብቻ አይደለም፤ በነገዋና በከነገ ወዲያዋ ኢትዮጵያ ላይ ጭምር የምንወስነው ውሳኔ ነው፡፡ የኛ የመሪዎቹ ውሳኔ ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ዜጋ ውሳኔ በታሪክ የሚመዘገብ ነው፡፡

ይሄንን አስቸጋሪ ጊዜ ልናልፈው የምንችለው በአካል ተራርቀን በመንፈስ ግን አንድ ሆነን ከቆምን ብቻ ነው፡፡
የያንዳንዳችን ሀብት የሁላችን፣ የእያንዳንዳችንም ችግር የሁላችን መሆን አለበት፡፡ አንዱ በልቶ ሌላው ተርቦ፣ አንዱ ሠርቶ ሌላው ሥራ አጥቶ፣ አንዱ መኖሪያ አግኝቶ ሌላው ውጭ አድሮ፣ አንዱ አትርፎ ሌላው ከሥሮ ይሄንን ችግር ለማለፍ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ይህ ችግር የመጣው በህልውናችን ላይ በመሆኑ፡፡ ይህ ችግር የተጋረጠው ሰው ሆኖ በመኖርና ባለመኖር ላይ በመሆኑ፡፡

መንግሥት ችግሩን በደረሰበት ልክ ለመቋቋም ተዘጋጅቷል፡፡ የምንወስዳቸው ውሳኔዎች ክብደት እንደ ችግሩ ክብደት የሚወሰን ነው፡፡ ታሪክ እዚህ አድርሶናል፡፡ ሀገርና ትውልድ በእጃችን ላይ ነው፡፡ በዚህ ዘመን በምንሠራው ሥራ ወይ እንመሰገናለን ወይ እንወቀሳለን፡፡ ከምንም በላይ ግን በጊዜውና በዐቅማችን ማድረግ ያለብንን ካላደረግን የበለጠ እንወቀሳለን፡፡ ይህ ደግሞ ሁላችንንም ኢትዮጵያውያንን የሚመለከት ነው፡፡ ከተረፍን አብረን ነው፡፡ ከከሠርንም አብረን ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣጡ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል፡፡ ይህም በሕገ መንግሥቱ ዐንቀጽ 93 መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ይሄንን መሳይ ዐዋጅ ብዙ ሀገሮች ካወጁ ሰንብተዋል፡፡ እኛ እስክንዘጋጅና ሁኔታው የግድ እስኪለን ጠብቀናል፡፡

ጊዜው ሲጠይቅ ግን ዐውጀናል፡፡ ሀገርን ለማዳንና ትውልድን ለመታደግ ከዚህ በላይ ልንወስን እንደምችልም መታወቅ አለበት፡፡ ዜጎቻችንም ከዚህ በላይ ግዴታቸውን ለመወጣት ወገባቸውን አጥብቀው መጠበቅ አለባቸው፡፡

በዚህ ወቅት ሁላችሁም ችግሩን ለመቋቋም ከሚሠሩት አካላት ጋር አብራችሁ እንድትቆሙ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ችግሩን ለማባባስ የሚሠሩ ካሉ ግን፣ በሕጉ መሠረት የማያዳግም ርምጃ እንወስዳለን፡፡
ወገኖቼ፤

ኢትዮጵያውያን የሚያምርብን መረዳዳቱና መደጋጋፉ ነው፡፡ ድኾችን እንርዳ፡፡ በአካባቢያችን ላሉት ዐቅመ ደካሞች እንድረስላቸው፡፡ የቤት ተከራዮቻችንን ዕዳ እንካፈላቸው፡፡

ከቻልን አናስከፍላቸው፤ ካልቻልን ቅናሽ እናድርግላቸው፡፡ ያም ካልሆነ ይህ ጊዜ እስኪያልፍ እንታገሣቸው፡፡ በዚህ ወቅት ተከራዮችን ከቤት ማስወጣት ፈጣሪም፣ ታሪክም ሕግም ይቅር የማይሉት ወንጀል ነው፡፡ ማናችን አልፈን ማናችን እንደምንተርፍ ለማናውቅበት ጊዜ ከመተባበር የተሻለ መሻገሪያ የለንም፡፡ የግል ባለሀብቶች የሠራተኞቻቸው ሕይወት እንዲያስጨንቃቸው አደራ እላለሁ፡፡ መንግሥት የኢኮኖሚ ችግሮቻችንን ለመፍታት አስፈላጊውን ሁሉ እየወሰነ አብሯችሁ እንደሚሆን በዚህ አጋጣሚ እገልጥላችኋለሁ፡፡

ለሌሎች ወገኖቻቸውና ለሀገራቸው ሲሉ ቤታቸውን፣ ሆቴላቸውን፣ አዳራሾቻቸውን፣ የእምነት ተቋሞቻቸውን፣ መኪኖቻቸውን፣ ገንዘባቸውንና እህላቸውን የሰጡ ዜጎቻችንን ስናይ ይሄንን አስቸጋሪ ወቅት ከፈጣሪ ጋር ሆነን ልናልፈው እንደምንችል ርግጠኞች እንሆናለን፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከወገኖቻቸው መከራ ለማትረፍ የሚሽቀዳደሙ፣ ከመከራ እንኳን የማይማሩ ሰዎችን ስናይ መንገዱ ከባድ እንዳይሆንብን እንሠጋለን፡፡ በጎ አድራጊዎችን የምናመሰግነውን ያህል መንገዳችንን ይበልጥ ፈታኝ የሚያደርጉብንን ስግብግቦች ግን ለሕዝብና ለሀገር ስንል አስተማሪ የሆነ ቅጣት ለመቅጣት እንገደዳለን፡፡

የሕክምና ባለሞያዎቻችንን በሚቻለው ሁሉ እንርዳ፡፡ ያለ እነርሱ ግንባር ቀደምነት ትግሉን ልናሸንፍ አንችልም፡፡ የሕክምና ባለሞያዎችን ማክበር፣ ማመስገንና በጉዟቸው ሁሉ መተባበር ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል፡፡

ለሕክምና ባለሞያዎች ተገቢውን ሁሉ አለማድረግ እጅን በእጅ እንደመቁረጥ ነው፡፡ ከእነርሱ በተጨማሪ የመከላከያ አባላት፣ የፖሊስ ሠራዊት አባላት፣ የኤሌክትሪክ ኃይልና የውኃ አቅርቦት እንዳይስተጓጎል የሚሠሩ ባለሞያዎች፣ የሚዲያ ባለሞያዎች፣ የመገናኛ መሥመሮቻችን ላይ 24 ሰዓት የሚያገለግሉ ዜጎች፣ እኛ ቤት እንድንውል እነርሱ ውጭ የሚውሉ ሠራተኞች ተገቢው ምስጋናና ድጋፍ ከቤተሰባቸውም፣ ከማኅበረሰባቸውም ያስፈልጋቸዋል፡፡

በዚሁ አጋጣሚ አርሶ አደሮቻችን የበልግ ወቅት እንዳያልፍብን ራሳቸውን ከቫይረሱ እየተጠነቀቁ በምርት ሥራ ላይ ጠንክረው እንዲሳተፉ አደራ እላቸዋለሁ፡፡ ከቫይረሱ ባልተናነሰ የእርሻ ምርት መቀነስና የእርሻ ምርት አለመኖር ሀገራችንንና ሕዝቧን ይጎዳል፡፡ እናንተ ሀገር መጋቢዎች ስለሆናችሁ፣ እየተጠነቀቃችሁ ካለፈው የተሻለ ምርት ለማምረት ትጉ፡፡ መንግሥትም አስፈላጊውን ሁሉ ሞያዊና ድጋፍ ያደርግላችኋል፡፡

የኢንዱስትሪ ምርቶቻችንም ፈጽመው መቆም የለባቸውም፡፡ ለሠራተኞቻችን ሕይወት እየተጠነቀቅን፣ በወረርሽኙ ምክንያት የሚያጋጥመንን ተግዳሮት ሁሉ እየተቋቋምን በፋብሪካ ምርቶች ላይ የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናድርግ፡፡ ከበተለይም ከውጭ የምናመጣቸውን ምርቶች ለመተካት ለሚደረገው ጥረት መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግላችሁ እገልጥላችኋለሁ፡፡ በተለይ ግን በምርት ዝውውር ጊዜ ከፍተኛ የሆነውን የመጨረሻ ጥንቃቄ እንዲደረግ ለአፍታም ቢሆን እንዳትዘነጉት ይሁን፡፡

ይህ ጊዜ ያልፋል፡፡ ሀገራችን ከዚህ የሚስተካከሉና ከዚህም የሚብሱ ፈተናዎችን አልፋለች፡፡ ዓለማችን በየዘመናቱ የከፉ ተግዳሮቶችን አልፋ ነው እዚህ ዘመን የደረሰችው፡፡

የሚሰጡንን መመሪያዎች በሚገባ እናክብር፣ የጤና ባለሞያዎች የሚሉንን ለሕይወታችን ስንል እንስማ፡፡ በኮሮና አይቀለድም፡፡ ጉዳዩ ከመኖርና ካለመኖር ጋር የተያያዘ ነው፡፡

ይሄንን ፈተና ለማለፍ ባለ ሦስት መዓዝን ትብብር ያስፈልገናል፡፡ ወደ ጎን እኛ እርስ በርሳችን፡፡ እያንዳንዳችን ደግሞ ከፈጣሪያችን ጋር፡፡ እኔ ከሌላው ወገኔ ጋር፣ ሌላው ወገኔ ከእኔ ጋር፣ እኔና ሌላው ወገኔ ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት መሥመር መቼም መቋረጥ የለበትም፡፡

በርትተንና ተረባርበን የሚጠበቅብንን እናድርግ፣ ጸንተንና በተሰበረ ልብ ሆነን ወፈደ ፈጣሪ እንለምን፡፡ ፈጣሪ ከእኛ ጋር ነው፡፡ መከራውን ያቀልልናል፤ ፈተናውን ያሳልፈናል፤ ማዕበሉን ያሻግረናል ብለን እናምናለን፡፡

የሃይማኖት አባቶች ያዘዙንን ጥንቃቄ እየፈጸምን ያዘዙንንም ጸሎት ተግተን እንጸልይ፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
መጋቢት 30/ 2012 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

National Committee Receives Donations to fight COVID-19

H.E. Gedu Andargachew, Minister of Foreign Affairs of Ethiopia, received monetary and in-kind donations on behalf of the National Resource Mobilization Committee, from various organizations to fight the COVID-19 pandemic.

Accordingly, the minister received:

-USD $100,000 from the Intergovernmental Authority on Development (IGAD) staff members. According to Commander Abebe Muluneh, IGAD Security Sector Program Director, the donation is part of the IGAD Staff members’ initiative to contribute USD $100.000.00 to each member states to help them fight the COVID-19 scourge;

-USD $1m from Ethiopian Diaspora Trust Fund (EDTF) handed over by Mr. Eyesuswork Zafu, Chairman of EDTF Board of Directors,

-Estimated 4.5 m (in-kind donation) from HOPE Enterprises,

-2 m Ethiopian Birr from Organization for Rehabilitation and Development in Amhara (ORDA),

-1.2 m Ethiopian Birr from VSO in Ethiopia,

-541.808 Ethiopian Birr from Pathfinder International Ethiopia,

-400,000 Ethiopian Birr from “Ahun Fiker” Organization,

-300,000 Ethiopian Birr from ‘’Ras Agez’’ (Women self-help group in Ethiopia),

-100,000 Ethiopian Birr from Organization for Welfare and Development,

On the occasion, Mr. Gedu appreciated the initiative taken by all of the organizations to be part of the joint approach of fighting the pandemic.

He also underscored that such donations would add muscles to the Government and people of Ethiopia in their fight to limit the spread of the virus and minimize its effects.

H.E. Ambassador Birtukan Ayano, a State Minister of the Foreign Affairs of Ethiopia and H.E. Dr. Eyob Tekalgn Tolina, a State Minister of Ethiopia’s Ministry of Finance attended the occasion representing the Resource Mobilization Committee that was set up to fight COVID-19.