Procuration

እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒ አያይዘው ይላኩ፡፡

  • እንዲረጋገጥልዎ የፈለጉት የውክልና ሰነድ ሆኖ ኢትዮጵያዊ/ት ሆነው የአገልግሎት ዘመኑ ያላበቃ ፓስፖርት ወይም ያገልግሎት ዘመኑ ያላበቃ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ካለዎት የውክልና ሰነዱን ኖተራይዝ አስደርገው ከሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች ጋር በቀጥታ ወደ ኤምባሲው መላክ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን አገልግሎቱ የፀና የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ወይም አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከሌለዎት ውክልናውን በአማርኛና በእንግሊዘኛ ተጽፎ ኖተራይዝ በማድረግ በመጀመሪያ ባሉበት አገር ኦፊስ ቀጥሎ በምትገኙበት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተረጋገጠ በሁዋላ ወደ ኤምባሲያችን መላክ ይኖርብዎታል፡፡
  • ማንኛውም ለማረጋገጥ የሚቀርብ ዶክመንት ከቤኔሉክስ አገሮች የመነጩ (የተሰጠ) ከሆነ (ለምሳሌ – ያላገቡ መሆነዎትን የሚያረጋግጥ፣ የልደት የምስክር ወረቀት እና የመሳሰሉትን …) መጀመሪያ ካሉበት አካባቢ አገር ኦፊስ በመሄድ ዶኩመንቱን ካረጋገጡ በኋላ በምትገኙበት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተረጋገጠ በኋላ ወደ ኤምባሲያችን መላክ ይኖርበታል፡፡
  • ለማረጋገጥ የሚፈልጉት ዶኩመንት ከኢትዮጵያ የመነጨና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ከሆነ በቀጥታ ወደ ኤምባሲያችን በመላክ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ፣
  • ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number DHL TNT Bpost Express mail ባለው መሆን ይገባዋል፡፡ የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱም ሆነ የተዘጋጀለዎት ሰነድ ወደ እርሶ ተመላሽ ለመደረጉ ባለዎት የፖስታ Tracking Number በመጠቀም ማጣራት ሰለሚችሉ ይህንኑ መረጃ ለማረጋገጥ ወደ ኢምባሲው መደወል አይጠበቅብም፡፡

Télécharger le formulaire

S’il vous plaît remplir les formulaires soigneusement comme décrit ci-dessous et nous les envoyer

  • Si vous êtes titulaire d’un passeport éthiopien valide ou d’une carte d’identité d’origine éthiopienne en cours de validité, vous pouvez envoyer un document notarié de procuration directement à l’ambassade. Si ce n’est pas le cas, votre document de procuration devrait être authentifié par votre bureau d’État, puis par les pays du Benelux.
  • Tous les documents provenant du Benelux, tels que Adoption, Marque, Droits de propriété, Décisions judiciaires, Certificats de naissance, Certificats de Mariage ou de Divorce, etc. doivent être authentifiés par votre Bureau d’Etat puis par le Département d’Etat avant de faire votre demande à l’Ambassade.
  • Tous les documents provenant d’Éthiopie doivent être authentifiés par le Ministère des Affaires étrangères de l’Éthiopie.
  • Toutes les demandes doivent être envoyées par e-mail avec une enveloppe ayant un numéro de suivi. Les demandes doivent également comporter une enveloppe de réponse pré-affranchie (DHL TNT Bpost Express) et portant un numéro de suivi. Vous n’avez pas besoin d’appeler l’ambassade pour vérifier si votre demande a été reçue ou renvoyée à vous puisque vous avez la possibilité de la suivre en ligne sur le site web de la société postale concernée.

 

የውክልና አገልግሎቶች

ሀ. የኢትዮጵያ ዜግነት ላላቸው እና የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለያዙ የውጭ ሀገር ዜጎች መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1 በኖታሪ ፓብሊክ የተሰጠዎትን ውክልና በአገሩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አረጋግጠው መላክ
2 በዜግነት ኢትዮጵያዊ/ት አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ኮፒ ፣ በአገሩ መንግስት የተሰጥዎት የመኖሪያ ፈቃድ መታወቂያ ኮፒ ፤ በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ /ቢጫ/ ካለዎት የታደሰ የመታወቂያ ካርድ ኮፒ
3 በዜግነት ኢትዮጵያዊ ከሆኑ በቤኔሉክስ አገሮች የሚኖሩበትን ስታተስ የሚያሳይ የመኖሪያ ፍቃድ ወይም መታቂያ ካርድ ከሌለዎት የስራ ፍቃድ ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይገባል ፣
4 የአገልግሎት ክፍያ 55.80 ዩሮ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ባንክ ማስገባት /Diposit Order/
6 አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው DHL TNT Bpost Express mail አብሮ መላክ ፣

ለ. የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለሌላቸው ወይም አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1 ውክልናው በኖታሪ ፓብሊክ አሰርተው የተሰጠዎትን ውክልና በአገሩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አረጋግጠው መላክ
2 የአገልግሎት ክፍያ 85.50 ዩሮ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ባንክ ማስገባትዎ /Diposit Order/ አብሮ ሙላክ አይርሱ ፣
4 አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው DHL ፣TNT፣ Bpost Express mail ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣

Procuration (Wikilina), décisions de justice et documents pécuniaires

A. Pour les Éthiopiens et les titulaires de l’origine éthiopienne

  1. Document notarié par un notaire reconnu;
  2. Une copie du passeport éthiopien valide (pour le détenteur du passeport éthiopien); Copie de la carte d’identité d’origine éthiopienne valide (pour les étrangers qui détiennent une carte d’identité d’origine éthiopienne);
  3. Copie d’une carte de résident (pour le détenteur d’un passeport éthiopien);
  4. Frais de service 53.10 euros par document pour chaque authentification payable sur le compte bancaire de l’Ambassade
  5. Un formulaire de demande rempli (télécharger le formulaire)
  6. Une enveloppe de retour adressée à votre adresse avec un numéro de suivi (courrier DHLTNT Bpost Express).

B. Pour ceux qui n’ont pas de passeport éthiopien ou de carte d’identité éthiopienne valide et pour les autres ressortissants

  1. Document authentifié par le Secrétariat d’État dans lequel réside le demandeur, et par États du Benelux concerné.
  2. Frais de service de 85.50 euros par document payable sur le compte bancaire de l’Ambassade
  3. Un formulaire demande rempli (télécharger le formulaire)
  4. Une enveloppe de retour adressée à votre adresse avec un numéro de suivi (courrier DHLTNT Bpost Express).