Power of Attorney

እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒ አያይዘው ይላኩ፡፡

  • እንዲረጋገጥልዎ የፈለጉት የውክልና ሰነድ ሆኖ ኢትዮጵያዊ/ት ሆነው የአገልግሎት ዘመኑ ያላበቃ ፓስፖርት ወይም ያገልግሎት ዘመኑ ያላበቃ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ካለዎት የውክልና ሰነዱን ኖተራይዝ አስደርገው ከሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች ጋር በቀጥታ ወደ ኤምባሲው መላክ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን አገልግሎቱ የፀና የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ወይም አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከሌለዎት ውክልናውን በአማርኛና በእንግሊዘኛ ተጽፎ ኖተራይዝ በማድረግ በመጀመሪያ ባሉበት አገር ኦፊስ ቀጥሎ በምትገኙበት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተረጋገጠ በሁዋላ ወደ ኤምባሲያችን መላክ ይኖርብዎታል፡፡
  • ማንኛውም ለማረጋገጥ የሚቀርብ ዶክመንት ከቤኔሉክስ አገሮች የመነጩ (የተሰጠ) ከሆነ (ለምሳሌ – ያላገቡ መሆነዎትን የሚያረጋግጥ፣ የልደት የምስክር ወረቀት እና የመሳሰሉትን …) መጀመሪያ ካሉበት አካባቢ አገር ኦፊስ በመሄድ ዶኩመንቱን ካረጋገጡ በኋላ በምትገኙበት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተረጋገጠ በኋላ ወደ ኤምባሲያችን መላክ ይኖርበታል፡፡
  • ለማረጋገጥ የሚፈልጉት ዶኩመንት ከኢትዮጵያ የመነጨና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ከሆነ በቀጥታ ወደ ኤምባሲያችን በመላክ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ፣
  • ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number DHL TNT Bpost Express mail ባለው መሆን ይገባዋል፡፡ የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱም ሆነ የተዘጋጀለዎት ሰነድ ወደ እርሶ ተመላሽ ለመደረጉ ባለዎት የፖስታ Tracking Number በመጠቀም ማጣራት ሰለሚችሉ ይህንኑ መረጃ ለማረጋገጥ ወደ ኢምባሲው መደወል አይጠበቅብም፡፡

የክፍያ መረጃ (payment information)፡

ተ.ቁ የትምህረት፣ የልደት የጋብቻ፣ መንጃ ፈቃድና የመሣሠሉት

የምስክር ወረቀቶች  ( certificates of Educational, birth, Driving and other documents)

በዩሮ €
1 ኢትዮጵያውያኖች (For Ethiopians) 53.10
2 ለውጭ ዜጐች (For non Ethiopian)  81

 

ተ.ቁ የፍርድ ቤት ውሣኔዎችናቢዝነስ ፣ ሀብት ነክ ጉዳዮችየሚመለከቱ ሰነዶች ሙሉ ውክልና ( for Power of Attorney , cases  related court and property) በዩሮ €
1 ኢትዮጵያውያኖች (For Ethiopians) 55.80
2 ለውጭ ዜጐች (For non Ethiopian) 85.50

 

Power of Attorney Sample Document

Please fill the forms carefully as described below and send them to us

  • If you are a holder of valid Ethiopian Passport or of valid Ethiopian Origin ID card, you can send the notarized document of Power of Attorney directly to the Embassy. If not, your Power of Attorney document should be authenticated by your State Office and the Benelux Countries.
  • All documents originating in the Benelux, such as Adoption, Trade Mark, Property Rights, Court Decisions, Birth Certificates, Marriage or Divorce Certificates, etc) must be authenticated by your State Office and then by Departement of State prior to applying at the Embassy.
  • All documents originating in Ethiopia should be authenticated by Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia.
  • All applications must be sent via e-mail with an envelope which has a TRACKING NUMBER. The applications must also have a self-addressed, prepaid (DHL TNT Bpost Express mail ) return envelop which has a tracking Number. You don’t have to call the Embassy to check whether your application has been received or returned back to you since you have the option to track it online at the respective mailing company’s website.

Click here to download the form

የውክልና አገልግሎቶች

ሀ. የኢትዮጵያ ዜግነት ላላቸው እና የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለያዙ የውጭ ሀገር ዜጎች መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

  1. በኖታሪ ፓብሊክ የተሰጠዎትን ውክልና በአገሩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አረጋግጠው መላክ
  2. በዜግነት ኢትዮጵያዊ/ት አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ኮፒ ፣ በአገሩ መንግስት የተሰጥዎት የመኖሪያ ፈቃድ መታወቂያ ኮፒ ፤ በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ /ቢጫ/ ካለዎት የታደሰ የመታወቂያ ካርድ ኮፒ
  3. በዜግነት ኢትዮጵያዊ ከሆኑ በቤኔሉክስ አገሮች የሚኖሩበትን ስታተስ የሚያሳይ የመኖሪያ ፍቃድ ወይም መታቂያ ካርድ ከሌለዎት የስራ ፍቃድ ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይገባል ፣
  4. የአገልግሎት ክፍያ 55.80 ዩሮ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ባንክ ማስገባት /Diposit Order/
  5. አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው DHL TNT Bpost Express mail አብሮ መላክ ፣

ለ. የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለሌላቸው ወይም አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

  1. ውክልናው በኖታሪ ፓብሊክ አሰርተው የተሰጠዎትን ውክልና በአገሩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አረጋግጠው መላክ
  2. የአገልግሎት ክፍያ 85.50 ዩሮ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ባንክ ማስገባትዎ /Diposit Order/ አብሮ ሙላክ አይርሱ ፣
  3. አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው DHL ፣TNT፣ Bpost Express mail ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣

Power of Attorney (Wikilina), Court Decisions and Pecuniary Documents

A. For Ethiopians and Holders of Ethiopian Origin ID

  1. Notarized Document by a recognized notary office;
  2. Copy of valid Ethiopian passport (for Ethiopian passport holder); Copy of Valid Ethiopian origin ID Card (for foreigners who are holding Ethiopian origin ID card);
  3. Copy of a Resident Card ( for Ethiopian passport holder);
  4. Service fee 55.80 euro per document for each authentication payable to the Embassy of Ethiopia in Deposit order;
  5. A completed application form (click here to download the form)
  6. A self-addressed return envelope which has a tracking number (DHLTNT Bpost Express mail ) with it.

B. For those who don’t have valid Ethiopian Passport or Ethiopian origin ID Card and for Other Nationals

  1. Authenticated document by the State Secretary Office in which the applicant is residing and then authentication of the same document by the Benelux States.
  2. A service fee of 85.50 euro- per document payable to the Embassy of Ethiopia in Deposit Order
  3. A completed application (click here to download the form)
  4. A self-addressed return envelope which has a tracking number (DHLTNT Bpost Express mail ) with it.