Laissez-passer (የይለፍ ሰነድ)

ሊሴ ፓሴ መግቢያ የጉዞ ሰነድ ለሚጠይቁ

  1. ለአስቸካይ ጉዞ ወደ አገር ቤት ለመሄድ የአገልግሎት ጊዜውን ያበቃ ፓስፖርት ለማሳደስ በቂ ጊዜ የሌላቸው በተለያየ አስቸኳይ ምክንያት ወደ አገርቤት ለመጓዝ የፈለጉ ሌሴ ፓሴ መጠየቅ።
  2. ሊሴ ፓሴው ለአንድ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መግቢያ ብቻ የሚያገለግል በመሆኑ ሲመለሱ ከኢትዮጵያ ፓስፖርት ማውጣት እንደሚጠበቅ።
  3. የፓስፖርትና የሊሴ ፓሴ ማመልከቻ በአንድ ላይ ማቅረብ ወይም የፓስፖርትዎ ማመልከቻ ከኤምባሲው ወደ አገር ቤት ከተላከ ከአንድ ወርና ከዚያ በላይ ሳይሆን ሊሴ ፓሴ ማመልከት አይቻልም። ነገር ግን ኢምባሲው ማመልከቻዎን አገር ቤት ከተላከ አንድ ወርና ከዚያ በላይ ከሆነና ፓስፖርቱን ሳይረከቡ የጉዞዎ ቀን ከደረሰ ሊሴ ፓሴ ወስደው አገር ቤት ሲደርሱ የከፈሉበትን ደረሰኝ ይዞው ፓስፖርት ከኢሚግሬሽን መረከብ የሚችሉ መሆኑን።
  4. ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው DHL TNT BPOST EXPRESS MAIL መሆን ይገባዋል፡፡ የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱም ሆነ የተዘጋጀለዎት ሰነድ ወደ እርሶ ተመላሽ ለመደረጉ ባለዎት የፖስታ Tracking Number በመጠቀም ማጣራት ሰለሚችሉ ይህንኑ መረጃ ለማረጋገጥ ወደ ኢምባሲው መደወል አይጠበቅም።

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

  1. ሁለት (2) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮ የሚታይ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
  2. አገልግሎቱ ያበቃዉን ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ ኮፒ ማቅረብ
  3. በቤኔሉክስ አገሮችየሚኖሩበትን ስታተስ የሚያሳይ የመኖሪያ ፍቃድ ወይም የስራ ፍቃድ ማስረጃ ኮፒ ማቅርብ ፣
  4. የአገልግሎት ክፍያ 117.60 ዮሮ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ አካውንት BANK ACCOUNT IBAN: BE53 3631 2148 4153 ማስገባት
  5. የሊሴ ፓሴ መጠየቂያ ቅጽ መሙላት Laissez-passer Form
  6. የተለየ ችግር ያለባቸው አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው DHL TNT BPOST EXPRESS መላክ ይጠበቃል ፣ አሸራ መስጠት የሚጠበቅባቸው ማስረጃ ይዞው በግንባር መቅርብ ይገባል ፣

Latest News