ክብርት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ Heath and Prosperity through Immunization ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ ተሳተፉ

ክብርት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ Heath and Prosperity through Immunization ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ ተሳተፉ፣
ጁን 25 ቀን 2025 ዓ.ም. Gavi the Vaccine Alliance ከአውሮፓ ህብረት እና ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ባዘጋጁት ፣ ከ2026–2030 ቢያንስ 8 ሚሊዮን ህይወትን አደጋ ለመታደግ ፣ ዓለማችንን ከግጭት እና ከአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል ያለመ የቃል-መግባት (ገቢ ማሰባሰቢያ) ጉባኤ ላይ አገራችን በክብርት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኩል ተሳትፎ አድርጋለች።
በቃል መግባት ጉባዔው 10 የሀገር መሪዎች እና 24 ሚኒስትሮችን ጨምሮ 55 የለጋሽ እና ተባባሪ ሀገራት ተወካዮች እንዲሁም የባለብዙ ወገን ተቋማት ፣ሲቪል ማህበረሰብ ፣የግሉ ሴክተር እና የክትባት ኢንዱስትሪ መሪዎች ተሳትፈዋል።
ክብርት ሚኒስትር በጉባዔው ባስተላለፉት መልዕክት በክትባት አቅርቦት ላይ መዋዕለ ንዋይን በማፍሰስ የተሻለ ነገ እንዲፈጠር ጥሪ አስተላልፈዋል።
በጉባዔው ከ9 ቢሊዮን ዶላር በላይ አጋር አገራትና ለጋሾች ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። በሚቀጥሉት ወራት ተጨማሪ ለጋሾች ቃል እንደሚገቡ ይጠበቃል። ጉባኤው በ Gavi African Vaccine Manufacturing Accelerator በኩል የአፍሪካ የክትባት ሉዓላዊነትን እንደሚደግፍ አረጋግጧል።
ክብርት ዶ/ር መቅደስ ከጉባዔው ማጠናቀቂያ በኋላ በብራሰልስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ በመገኘት ከዲፕሎማቶች ጋር ውይይት አድርገዋል፣ በጋራ ስለሚሰሩ ስራዎችም ማብራሪያ ሰጥተዋል።