የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አፈጻጸም መመሪያ (የልደት፣ጋብቻ፣ፍቺ እና ሞት) የምስክር ወረቀት
በኢትዮጵያ ኤምባሲ ብራስልስ የወሳኝ ኩነት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፣
መስፈርቶች እና ደጋፊ ማስረጃዎች፣
1. የልደት ምዝገባ
የልደት ምዝገባ ለማከናወን መሟላት የሚገባቸው ደጋፊ ማስረጃዎች እና መስፈርቶች፡-
1.1. አስመዝጋቢው ጊዜው ያላለፈበት የነዋሪነት/ብሄራዊ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመኖሪያ ፍቃድ ወይም ስደተኝነቱን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
1.2. በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ልደቱ የተከሰተው በጤና ተቋም ከሆነ አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን የልደት ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
1.3. የልደት አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን የልደት ማሳወቂያ ቅጽ ማቅረብ አለበት፡፡ ሆኖም ምዝገባው ከመጀመሩ በፊት የተከሰተን ልደት ምዝገባን አይጨምርም።
1.4. የህጻኑ አሳዳጊ ወይም ተንከባካቢ ልደቱን ለማስመዝገብ ሕጋዊ የአሳዳሪነት ወይም ተንከባካቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
1.5. ዕድሜው አስራ ስምንት ዓመትና በላይ የሆነ ስደተኛ ወላጆቹን የሚገልፅ ማስረጃ ከስደተኞች መረጃ ዳታ ቤዝ ላይ መረጃው የሌለ እንደሆነ ስደተኛውን በመጠየቅ መመዝገብ አለበት።
1.6. የልደት ምዝገባ አገልግሎት ክፍያ 53.10 ዩሮ ብቻ ነው።
2. የጋብቻ ምዝገባ
የጋብቻ ምዝገባ ለማከናወን መሟለት የሚገባቸው ደጋፊ ማስረጃዎች እና መስፈረቶች፡-
2.1. ተጋቢዎች ጋብቻ ለመፈፀም ማሰባቸውን እጅግ ቢዘገይ ጋብቻቸውን ለመፈፀም ከወሰኑበት ቀን ከአንድ ወር በፊት ለኢምባሲው ማስታወቅ አለባቸው፡፡ሆኖም ይህ ድንጋጌ በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስርዓት የሚፈፀም ጋብቻን አይመለከትም።
2.2. የክብር መዝገብ ሹሙ ጥያቄው በቀረበለት ቀን ከተጋቢዎቹ ጋር በመነጋገር ከወሰነ በኃላ በማግስቱ ጋብቻው የሚፈፀምበትን ቀን በመግለጽ አመቺ በሆነው መንገድ ለ15 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ማስታወቂያ ያወጣል።
2.3. ተጋቢዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
2.4. የተጋቢ ምስክሮች አገልግሎቱ ያላለፈበት የነዋሪነት/ብሄራዊ መታወቂያ ወይም የስደተኝነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም ሌላ ማንነትን ሊገልፅ የሚችል ማስረጃ መቅረብ አለበት።
2.5. ተጋቢዎች ከዚህ በፊት አግብተው የተፋቱ ከሆነ የፍቺ ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለባቸው።
2.6. ከ 6 ወር ወዲህ በተመሳሳይ ጊዜ የተነሱት ሁለት ሁለት 3 በ 4 የሆነ የተጋቢዎች ፎቶ-ግራፍ መቅረብ አለበት።
2.7. በባህላዊ ስርዓት የተፈፀመ ጋብቻ የተጋቢዎች ምስክሮች ወይም በጋብቻ ስርዓቱ ላይ የታደመ ሰው በክብር መዝገብ ሹሙ ፊት በአካል ቀርበው ፊርማቸውን ማኖር አለባቸው።
2.8. የተጋቢዎች የልደት ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለበት።
2.9. በሙሽራው በኩል 2 በሙሽሪት በኩል 2 በድምሩ 4 ምስክሮች መቅረብ አለባቸው፡፡ሆኖም በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 16 መሰረት የተፈፀመ ከሆነ ምስክሮችን በተመለከተ ያለው ክፍት ቦታ በሰረዝ (-) ይታለፋል።
2.10. ተጋቢው ስደተኛ ከሆነ የስደተኝነት እውቅና ያገኘ መሆን አለበት፡፡በማንኛውም ስርዓት የሚፈፀም ጋብቻ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት አለበት።
2.11. የጋብቻ ምዝገባ አገልግሎት ክፍያ 53.10 ዩሮ ብቻ ነው።
3. የፍቺ ምዝገባ
የፍቺ ምዝገባ ለማከናወን መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችና ደጋፊ ማስረጃዎች፡-
3.1. ፍቺው ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተፈፀመ መሆን አለበት።
3.2. የፍቺ አስመዝጋቢ ሆነው የሚቀርቡት ተፋቺዎች በጋራ ወይም ከተፋቺዎች አንዱ ወይም የተፋቺዎች ልዩ ውክልና ያለው መሆን አለበት።
3.3. ተፋቺው ስደተኛ ከሆነ የስደተኝነት እውቅና ያገኘ መሆን አለበት።
3.4. ፍቺው በፍርድ ቤት የተከናወነ መሆኑን የሚገልፅ የፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጭ መቅረብ አለበት።
3.5. ተፋቺዎች ፍቺውን ለማስመዝገብ ሲመጡ ጊዜው ያላለፈበት የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ወይም ማህበራዊ መታወቂያ ወይም ስደተኝነታቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
3.6. ቀደም ሲል የጋብቻ ምስክር ወረቀት የተሰጠ ከሆነ መመለስ አለበት።
3.7. የፍቺ ምዝገባ አገልግሎት ክፍያ 53.10 ዩሮ ብቻ ነው።
4. የሞት ምዝገባ
የሞት ምዝገባ ለማከናወን የሚያስፈልጉ ደጋፊ ማስረጃዎች፡-
4.1. ሞቱን ለማስመዝገብ ከጤና ተቋም የተሰጠ ማስረጃ መቅረብ አለበት።
4.2. የሟች ማንነት የሚገልጽ ማሰረጃ ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ወይም ሊሴ-ፓሴ ወይም ማህበራዊ መታወቂያ መቅረብ አለበት።
4.3. የሞት አስመዝጋቢ ከሀገሩ መንግሥት የሞት ምስክር ወረቀት ይዞ መቅረብ አለበት።
4.4. ሞቱ የሚመዘገበው በግለሰቡ መጥፋት ውሳኔ ምክንያት ከሆነ የፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ መቅረብ አለበት።
4.5. የሞት ምዝገባ አገልግሎት ክፍያ 53.10 ዩሮ ብቻ ነው።
Latest News
- H.E. Ambassador Eshete Tilahun discussed with the Private Sector Representatives Ambassador Eshete and his team confered with the Director of Chamber of Commerce, Industry and Agriculture for Belgium, Luxembourg, Africa, the Caribbean, and the Pacific...
- Ambassador Eshete Tilahun met with Ambassador Jeanne CrauserNovember 22, 2025Ambassador Eshete Tilahun met with Ambassador Jeanne Crauser ——————————————————— H.E. Ambassador Eshete Tilahun received H.E. Mrs. Jeanne Crauser Ambassador of Luxembourg to Ethiopia, at the Chancey of the Embassy of Ethiopia for a bilateral meeting....
- H.E. Ambassador Eshete Tilahun met with Mrs. Naomi Meulemans, Head of Heritage Collections at the Africa Museum on 20 November 2025.November 22, 2025H.E. Ambassador Eshete Tilahun met with Mrs. Naomi Meulemans, Head of Heritage Collections at the Africa Museum on 20 November 2025. The Ambassador received briefings and then discussed on ways of co-organizing exhibition and public...
- Ms. Julie Blavier, daughter of the late Jean Paul Blavier, a former CEO of BGI Ethiopia and Castel Group, has handed over a collection of her father’s personal souvenir items to the Embassy of Ethiopia...
- H.E. Ambassador Eshete Tilahun confers with H.E. Ms. Beate GminderNovember 19, 2025H.E. Ambassador Eshete Tilahun confers with H.E. Ms. Beate Gminder =================================================== Ambassador Eshete Tilahun held a productive discussion with Ms. Beate Gminder, Director-General for Migration and Home Affairs (EU-DG HOME) on 18 November 2024. The...





