ክቡር አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን በኔዘርላንድ ሮተርዳም ከተማና አካባቢው ከሚኖሩ የሶማሌ ኮሚዩኒቲ አባላት ጋር ተወያዩ፣

ክቡር አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን በኔዘርላንድ ሮተርዳም ከተማና አካባቢው ከሚኖሩ የሶማሌ ኮሚዩኒቲ አባላት ጋር ተወያዩ፣
ክቡር አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን በኔዘርላንድ ሮተርዳም ከተማና አካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሶማሌ ኮሚዩኒቲ አባላት ጋር ዛሬ ነሃሴ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ተወያይተዋል። ውይይቱ በአገራዊ ሰላምና ዲሞክራሲ ግንባታ፣ በኢንቨስትመንት፣ ንግድና የልማት ተሳትፎ ያተኮረ ነበር።
በመድረኩ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና በአገራችን ወቅታዊ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ከኮሚዩኒቲው ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ክቡር አምባሳደር እሸቴ ገለፃ የሰጡ ሲሆን ዳያስፖራው ለአገራዊ ልማት ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያዊና ትውልደ-ኢትዮጵያዊ የሶማሌ ኮሚዩኒቲ አባላት የዳያስፖራውን ችግሮች በማቃለል ረገድ ሚሲዮኑ ለሚያደርገው ድጋፍ አመስግነው፣ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማጠናቀቂያ የቦንድ ግዢ እና የስጦታ ድጋፍ አድርገዋል። ለአገር አንድነትና ልማት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ እንደሚያስቀጥሉም ቃል ገብተዋል።
በመድረኩ ለክቡር አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን እና ኮሚኒቲውን ላጠናከሩ የዳያስፖራ አባላት ስጦታ እና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። በተጨማሪም ኬክ የመቁረስ ስነ-ስርዓት ተከናውኖ በድምቀት ተጠናቋል።
H.E. Ambassador Eshete Tilahun Engages with Ethiopian and Ethiopian-Origin Somali Diaspora in Rotterdam
Rotterdam, Netherlands – On 10 August 2025, H.E. Ambassador Eshete Tilahun held a fruitful discussion with members of the Ethiopian and Ethiopian-origin Somali diaspora community. The meeting focused on strengthening national development, investment, and trade, while also addressing good governance and Ethiopia’s political, economic, and social affairs.
The community expressed strong support for the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) through bond purchases and donations, reaffirming their commitment to the national flagship project. They also conveyed appreciation to the Embassy for its continued support and pledged to contribute further to Ethiopia’s unity and prosperity.
The event concluded with a vibrant ceremony, featuring the awarding of certificates to Ambassador Eshete Tilahun and diaspora members in recognition of their contributions to community strengthening.