ከእለታት አንድ ቀን ……….. በኢትዮጵያ ቤት
የማይቀርበት ልዩ የልጆች የመዝናኛ ዝግጅት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ ብራሰልስ ተዘጋጅቶላችኋል።
መቼ- ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም (August 16,2025) ከቀኑ 14፡00 እስከ 16፡00 ሰዓት
ምን አለ? በቤኔሉክስ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ- ኢትዮጵያውያን ልጆች ለኢትዮጵያ ያላቸውን ፍቅር ለማነቃቃት፣ ባህልና እሴትን እንዲያውቁ ለማድረግ፣ የልጆችን የፈጠራ ችሎታ በመጠቀም ለክረምት የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም ድጋፍ ለማሰባሰብ “ትንሽ እጅ ትልቅ ልብ” በሚል መሪ ሃሳብ ይህ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል።
ልጆችዎ የኢትዮጵያን ባህላዊ ጨዋታዎች ይታደማሉ፣ ከታዋቂው ኢትዮጵያዊ አርቲስት ንብረት ገላው (እከ ደከ) ጋር ይተዋወቃሉ፣ በፈረንሳይኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን “ላሜ ቦራ” መፅሃፍ በጸሐፊ ማዳም ሄኖኬ ኮርቴ ይነበባል፣ ለክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ልጆችዎ የበኩላቸውን ያበረክታሉ።
*ለመመዝገብ diaspora.brussels@mfa.gov.et ወይም +32 495 133 346 ላይ መልዕክት ያስቀምጡ
የት? Avenue de Tervuren 64 1040 Etterbeek, The Embassy of Ethiopia in Brussels