ID Card
08 September 2015: Announcement regarding ID cards (Amharic)
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ አገልግሎት
- የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለመረከብ ወደ ኤምባሲ በአካል መቅረብ የሚጠይቀውን አሰራር በተገልጋዩ ህብረተሰብ ላይ ምልልስ ለማስቀረት መመሪያውን በማሻሻል የተዘጋጀልዎትን የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ በፖስታ ቤት በኩል እንዲደርስ ተደርጓል ።
- አገልግሎቱን ለማግኘት ሲያመለክቱም ሆነ ሲረከቡ በአካል ወደ ኤምባሲ መቅረብ የለብዎትም። በመሆኑም በፖስታ ቤት በኩል ብቻ ተረክበን የምናስተናግድዎ በመሆኑ ወደ ኤምባሲው ሲልኩም ሆነ የተዘጋጀልዎትን የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ወደ እርሶ መልሰን ለመላክ Tracking Number ባለው DHL TNT BPOST EXPRESS አያይዘው ይላኩ። ኤምባሲው መታወቂያ ካርድዎ ከኢትዮጵያ እንደተረከበ በተቻለ ፍጥነት በላኩልን መመለሻ ፖስታ ይልክልዎታል። የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱም ሆነ ወደ እርሶ ለመመለሱ ባለዎት Tracking Number በመጠቀም ማወቅ ስለሚችሉ ወደ ኤምባሲ መደወል አይጠበቅም።
- የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርዱ ለ5 አመት የሚያገለግል ነው፡፡ መታወቂያ ካርዱን በጊዜው የአገልግሎት ዘመኑ ሳያበቃ መታወቂያ ካርዱን ያሳድሱ፡፡
- የአገልግሎት ዘመኑ እስካላበቃ ድረስ መታወቂያ ካርዱን በመያዝዎ ያለ ቪዛ ኢትዮጵያ ገብተው መውጣት ይችላሉ፡፡
- የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለማግኘት የጣት አሻራ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደም አዲሱን Machine Readable የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ሲወስዱ የጣት አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግም፡፡
- ከጉዞዎ ፣ ከታደሰ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ጋር በተያያዘ አገልግሎት ዘመኑ ከማለቀቁ በፊት ከ60 ቀናት አስቀድመው ማመልከት ይጠበቅብዎታል፡፡
- ኢምባሲው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለማዘጋጀት ተጨማሪ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ሲጠይቅ ፣ ከተነገረዎት በሳምንት ጊዜ ውስጥ ማስረጃውን ይላኩልን፡፡ ሆኖም ማስረጃውን እንዲልኩ ለ3ኛ ጊዜ ተገልጾልዎት ከሆነና በወቅቱ ካላቀረቡ ፋይልዎ ተመላሽ ተደርጎ እንደ አዲስ ማመልከት ይጠበቅቧታል፡፡
ሀ. አዲስ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ ለመጀመሪያ ጊዜ መታወቂያ ካርዱን ሲጠይቅ ቅፅ 1
ለ. የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኖሯቸው ለትዳር ጓደኛቸው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ቅፅ 2(ለጊዜው አገልግሎቱ ተቋርጧል)
ሐ. የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የአገልግሎት ዘመኑ በማለቁ ለማሳደስ ቅፅ 3
መ. በጠፋ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ምትክ ለሚጠይቁ ቅፅ 4
ሠ. በተበላሸ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ምትክ ሲጠይቁ ቅፅ 4
የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ ለመጀመሪያ ጊዜ መታወቂያ ካርዱን ሲጠይቅ
- መጠየቂያ ቅጽ-1 በሁለት ኮፒ መሙላትና ማቅረብ ፣
- የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት (አገልግሎቱ ቢያንስ ለ 6 ወራት የፀና ፓስፖርት) በሁለት ኮፒ
- በትውልድ ኢትዮጵያዊ መሆንን የሚያስረዳ ማስረጃ
- የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርትዎ ማንዋል (ሰማያዊ) ከሆነ መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ እንዲሁም አግባብ ካለው አካል የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የልደት ምስክር ወረቀት ጋር በሁለት ኮፒ ማያያዝ፤
- የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርትዎ አዲሱ ማሽን ሪዴብል ( ቡኒውን) ከሆነ መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና አገልግሎቱ የሚያበቃበት ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ፤
- አግባብ ካለው አካል የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የልደት ምስክር ወረቀት በሁለት ኮፒ፣ ወይም
- ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ ኢትዮጵያውያን ከሆኑ/ ከነበሩ የስጋ (Biological) ወላጆች የተገኘ የወራሽነት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣
- ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ በኢትዮጵያውያን ወላጆቹ በጉዲፈቻነት የተሰጠ ኢትዮጵያዊ እንደነበረ የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣
- ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት የሰው ወይም የሰነድ ምስክርነት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣
- ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨባጭ የሚያረጋግጥ አባቱ ወይም እናቱ ወይም ቅድመ አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነትን ይዞ የነበረ መሆኑን የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣
- የጣት አሻራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ አመልካቾች በግንባር መቅርብ፣ የተለየ አሳማኝ ምክንያት ያለው በአቅራቢያችሁ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ /Form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቱ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌለው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ። (click here to download Fingerprint capture form)
- ሶስት (5) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
6. የአገልግሎት ክፍያ 200 ዶላር በዕለቱ ምንዛሪ ዩሮ ሆኖለኢትዮጵያ ኤምባሲ ክፍያ ሲፈፀም / Diposit Order/ ማያዝ ፣
7. ምልልስ ለማሳጠር አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ( DHL TNT BPOST EXPRESS ) ፓስታ ከነመላኪያ አብሮ መላክ ፣
ለ. የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኖሯቸው ለትዳር ጓደኛቸው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ጠያቂ(አገልግሎቱ ለጊዜው ተቋርጧል)
1. መጠየቂያ ቅጽ-2 በሁለት ኮፒ በመሙላት ፣ የፀና የጋብቻ ማስረጃ ጋር ማቅረብ፣
2. የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የሚጠየቅለት ግለሰብ አገልግሎቱ ቢያንስ ለ6 ወር የፀና የውጭ አገር ፓስፖርት በሁለት ኮፒ
3. ከተሰጠበት ሀገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተረጋገጠ የጋብቻ ምስክር ወረቀት በሁለት ኮፒ (ጋብቻው ቢያንስ ለሁለት አመት የፀና መሆን ይኖርበታል)
4. መታወቂያው እንዲሰጥ የሚወሰነው ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙት የቃለ መሃላ ሰነድ ተያይዞ ሲቀርብ ነው፡፡ (Click here to download the form)
5. የባል/የሚስት አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ በሁለት ኮፒ
6. የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የሚጠየቅለት ግለሰብ ሶስት (5) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
7. የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የሚጠየቅለት ግለሰብ የጣት አሻራ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ /Form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቱ የጣት አሻር መውሰጃ ቅጽ ከሌለው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ። (click here to download Fingerprint capture form)
8. የአገልግሎት ክፍያ 200 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፍያ ማቅረብ /Deposit Order/
9. አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (DHL TNT BPOST EXPRESS ) ፖስታና መላኪያው አብሮ መላክ ፣
ሐ. የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የአገልግሎት ዘመኑ በማለቁ ለማሳደስ ጠያቂ
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርዱ ለ 5 አመት የሚያገለግል ይሆናል፡፡ የአገልግሎት ዘመኑ ሳያበቃ በጊዜው መታወቂያ ካርዱን ያሳድሱ፡፡
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ከ 6 ወር በላይ ሳያሳድሱ ከቆዩ ያላሳደሱበትን ምክንያትን የሚገልፅ ማመልከቻ አያይዘው ማቅረብ ፡፡
1. መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ በመሙላት (click here to download) መላክ ፣
2. አገልግሎት ዘመኑ ያበቃው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ዋናውንና በሁለት ኮፒ ፣
3. በትውልድ ኢትዮጵያዊ መሆንን የሚያስረዳ ተጨማሪ ማስረጃ ፣
3.1 አግባብ ካለው አካል የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የልደት ምስክር ወረቀት በሁለት ኮፒ፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርትዎ መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ ፣
3.2 ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ ኢትዮጵያውያን ከሆኑ/ ከነበሩ የስጋ (Biological) ወላጆች የተገኘ የወራሽነት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣
3.3 ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ በኢትዮጵያውያን ወላጆቹ በጉዲፈቻነት የተሰጠ ኢትዮጵያዊ እንደነበረ የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣ ወይም
3.4 ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት የሰው ወይም የሰነድ ምስክርነት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣ ወይም
3.5 ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨባጭ የሚያረጋግጥ አባቱ ወይም እናቱ ወይም ቅድመ አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነትን ይዞ የነበረ መሆኑን የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣
4. አገልግሎቱ ቢያንስ ለ6 ወር የፀና የውጭ አገር ፓስፖርት በሁለት ኮፒ ፣
5. አምስት (5) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮ የሚታይ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት) ፣
6. በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እድሳት ጥያቄ ከሆነ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ (Click here to download the form) ተያይዞ ሲቀርብ እንዲሁም አገልግሎቱ የፀና የባል ወይም የሚስት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ሁለት ኮፒ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል ፡፡
7. የጣት አሻራ ለመስጠት በግንባር መቅረብ የተለየ ችግር ያለው በአቅራቢያዎት በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ /Form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቱ የጣት አሻር መውሰጃ ቅጽ ከሌለው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ። (click here to download Fingerprint capture form) ነገር ግን ከዚህ በፊት የነበረዎት የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ማሽን ሪዴብል የነበረ ከሆነና አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ አሻራ መስጠት አይጠበቅም ፡፡
8. የአገልግሎት ክፍያ 200 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ማስገባት /Diposit Order/ማያያዝ ፣
9. አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (DHL TNT BPOST EXPRESS ) ከፖስታ ና ከነመላኪያው አብሮ መላክ ፣
መ. በጠፋ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ምትክ ለሚጠይቁ
1. መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ በመሙላት (click here to download) መላክ
2. የጠፋው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ ካለ ሁለት ኮፒ ፣
3. መታወቂያው ስለመጥፋቱ የጠፋ ስለመሆኑ ከፖሊስ ማስረጃ ጋር ፣ መቼ እና ከየት እንደተሰጠ የሚገልፅ ማመልከቻ ማቅረብ ፣
4. በትውልድ ኢትዮጵያዊ መሆንን የሚያስረዳ ተጨማሪ ማስረጃ
4.1. አግባብ ካለው አካል የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የልደት ምስክር ወረቀት በሁለት ኮፒ፣ ወይም
4.2. የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርትዎ መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ ወይም
4.3. ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ ኢትዮጵያውያን ከሆኑ/ ከነበሩ የስጋ (Biological) ወላጆች የተገኘ የወራሽነት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣ ወይም
4.4. ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ በኢትዮጵያውያን ወላጆቹ በጉዲፈቻነት የተሰጠ ኢትዮጵያዊ እንደነበረ የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣ ወይም
5. ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት የሰው ወይም የሰነድ ምስክርነት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣ ወይም
6. ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨባጭ የሚያረጋግጥ አባቱ ወይም እናቱ ወይም ቅድመ አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነትን ይዞ የነበረ መሆኑን የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣
5. የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት በሁለት ኮፒ
6. የጠፋው መታወቂያ ካርድ በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ ከሆነ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ የትዳር ጓደኛ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ (Click here to download the form) በሁለት ኮፒ እንዲሁም የባለቤቱ/ቷ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ኮፒ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡(አገልግሎቱ ለጊዜው ተቋርጧል)
7. የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ /Form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቱ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌለው በኤምባሲው በግንባር ቀርቦ የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ። (click here to download Fingerprint capture form) ነገር ግን ከዚህ በፊት የነበረዎት የኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ማሽን ሪዴብል የነበረ ከሆነና አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ አሻራ መስጠት አይጠበቅም ፡፡
8. አምስት (5) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮ የሚታይ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት) ፣
9. የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ክፍያ የፈፀሙትን / Deposit Order/ ማቅረብ ፣
9.1. በጠፋ ምትክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሰጥ 200 መደበኛው ዶላርና ከ20℅ በተበላሸ ምትክሲለወጥ 10℅ በዕለቱ ዩሮ ምንዛሪ ክፍያ መፈፀም ፤
9.2. በጠፋ ምትክ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሰጥ 200 መደበኛው ዶላርና ከ50℅ በዕለቱ ዩሮ ምንዛሪ ፤
9.3. በጠፋ ምትክ ለሶሰተኛ ጊዜና ከዚያ በላይ ሲሰጥ 200 ዶላር መደበኛውከ100℅ በዕለቱ ዩሮ ምንዛሪ ክፍያ መፈፀም ፤
10. አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ( DHL TNT BPOST EXPRESS ) ከፖስታ ጋር ከነመላኪያው መላክ ፣
ሠ. በተበላሸ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ምትክ ጠያቂ
1. መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ በመሙላት (click here to download the form) ማቅረብ ፣
2. የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት በሁለት ኮፒ ፣
3. የተበላሸው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ዋናውና ሁለት ኮፒ ጋር ፣
4. በትውልድ ኢትዮጵያዊ መሆንን የሚያስረዳ ተጨማሪ ማስረጃ ፣
5. በተበላሸ ምትክ ሲለወጥ መደበኛው ላይ 10℅ በዕለቱ ዩሮ ምንዛሪ ክፍያ መፈፀም ፣
5.1 አግባብ ካለው አካል የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የልደት ምስክር ወረቀት በሁለት ኮፒ፣ ወይም
5.2 የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርትዎ መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ ወይም ፣
5.3 ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ ኢትዮጵያውያን ከሆኑ/ ከነበሩ የስጋ (Biological) ወላጆች የተገኘ የወራሽነት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣
5.4 ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ በኢትዮጵያውያን ወላጆቹ በጉዲፈቻነት የተሰጠ ኢትዮጵያዊ እንደነበረ የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣
5.5 ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት የሰው ወይም የሰነድ ምስክርነት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣ ወይም
5.6 ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨባጭ የሚያረጋግጥ አባቱ ወይም እናቱ ወይም ቅድመ አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነትን ይዞ የነበረ መሆኑን የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ በሁለት ኮፒ ማቅረብ ይገባል ፣
6. የጣት አሻራ ነመስጠት በግንባር መቅረብ ወይምየተለየ ችግር አሳማኝ ምክንያት ካለ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ /Form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቱ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌለው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ። (click here to download Fingerprint capture form) ነገር ግን ከዚህ በፊት የነበረዎት የኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ማሽን ሪዴብል የነበረ ከሆነና አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ አሻራ መስጠት አይጠበቅም፡፡
7. አራት (4) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮ የሚታይ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት) ፣
8. የአገልግሎት ክፍያ 220 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ክፍያ የፈፀመ / Diposit Order/ማቅረብ ፣
9. አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው ( DHLTNT BPOST EXPRESS )ፖስታ ጋር ከነመላክያው መላክ ፣
Bank account IBAN: BE53 3631 2148 4153
Ethiopian Origin ID Cards
In order to obtain an Ethiopian Origin ID Card, please complete an application form and follow the instructions carefully
- In the past, all applicants were required to pick up the ID card in person at the Embassy. However, to give good services for the customer, the embassy has amended this directive so that you can receive your ID card by post of mail.
- Note that, the embassy will no longer give services for those who come in person. Send all the necessary documents via post office only with a tracking number (DHL By post Express mail). Accordingly, the embassy will send your ID card by your return mail as soon as we received it from Ethiopia Head Quarter.You don’t have to call the Embassy to check whether your application has been recieved or returned back to you since you have the option to track it online at the respective mailing company’s website.
- Ethiopian Origin ID Cards are valid for five years. Please renew your ID card before the expiry date.
- You do not have to apply for a visa if you have a valid Ethiopian Origin ID card and investments projects.
- Finger print is mandatory to have Ethiopian Origin ID Card. But those who have already submitted their finger prints upon receipt of an electronic ID card earlier are not required to submit their finger prints again.
- The Embassy also advise all applicants to submit their applications AT LEAST 60 DAYS AHEAD of their planned travel date or prior to applying for any other services that require a valid Ethiopian Origin ID Card.
- If the Embassy requests you to submit an additional document, please send it within a week. If you are informed for the third time to submit the necessary document and if you fail to submit the requested document, the Embassy shall be obliged to send your original document back to you and you will be requested to apply anew.
A. Requirements for foreign nationals of Ethiopian Origin to obtain Ethiopian Origin ID Card
- Fill out and submit two copies of Application forms. Click here to download the Application form.
- Two copies of valid passport from the country of naturalization. The passport must be valid more than 6 months.
- Two copies of Supporting documents showing Ethiopian Origin.
- If your old Ethiopian Passport was manual (Blue), Please attach Two copies of it (make sure to attach the pages which shows your name, your picture, date of issue and expiration date of the passport) and two copies of Birth certificate which is authenticated through Ethiopian Ministry of Foreign Affairs; or
- If your old Ethiopian Passport was machine-readable (Burgundy), Please attach Two copies of it (make sure to attach the pages which shows your name, your picture, date of issue and expiration date of the passport); or
- Two copies of Birth certificate which is authenticated through Ethiopian Ministry of Foreign Affairs; or
- Two copies of Court document authenticated by Ministry of Foreign Affairs showing that you are the legal inheritor. The inheritor should be the son/daughter of biological parents who are/were Ethiopians; or
- Two copies of adoption court document. The document should be authenticated by Ministry of Foreign Affairs. The adoption document must show that the adoptee was given to the adopter by Ethiopian parents and the adoptee even him/herself was an Ethiopian at the time of the adoption; or
- Two copies of the court document showing Ethiopian origin. The document should be authenticated by the Ministry of Foreign Affairs Addis Ababa; or
- Two copies of the court document showing that one of the applicant’s parents or grandparents were Ethiopians. The document should be authenticated by the Ministry of Foreign Affairs Addis Ababa.
- A fingerprint of the Applicant in person or if there is a personal problem (original and a copy). Please go to the nearest police station or to the companies authorized to take fingerprints. We prefer to have your fingerprint on their Fingerprint capture form. If not, you can use ours (click here to download the form)
- Five (5) recent, color passport size Photographs (with white background and the name of the applicant at the back of the photograph);
- Payment of $200.00 to the daily exchange euro in the form of deposit Order payable to the Embassy of Ethiopia Account in advance.
- A self-addressed return envelope which has a tracking number (DHL TNT Bpost Express mail) with it.
B. A holder of Ethiopian Origin ID card who applied for Ethiopian Origin ID Card for their Spouse( Temporarily suspended)
- Fill out and submit two copies of application form. Click here to download the form.
- Two copies of valid passport of the spouse in question. The passport must be valid at least for more than 6 months.
- Two copies of the marriage certificate. The marriage certificate should be authenticated through Ethiopian Ministry of Foreign Affairs Addis Ababa (If the marriage took place in Ethiopia) or authenticated through Benelux countries (If the marriage took place in the Benelux countries). The marriage should be valid for at least two years prior to the date of the application’s submission.
- The Ethiopian Origin ID Card is given only to Couples who can sign and submit a pledge form stating that their marriage is still valid. Click here to download the form.
- Two copies of valid Ethiopian Origin ID Card of the Applicant.
- Five (5) recent, color passport size photographs (with white background and name of the spouse in question at the back of the photograph).
- A fingerprint of the spouse in question (original and a copy) in person. If there is a personal problem please go to the nearest police station or to the companies authorized to take fingerprints. We prefer to have your fingerprint on their Fingerprint capture form. If not you can use ours (click here to download the form)
- Payment of $200 to daily euro rate in Diposit Order payable to Embassy of Ethiopia Account in Advance .
- A self addressed return envelope which has a tracking number (DHL TNT Bpost Express mail with it.
C. Renewal of Ethiopian Origin ID Card
A person who wishes to renew the Ethiopian Origin ID card should follow the steps outlined below. If your Ethiopian Origin ID card was expired for more than 6 months, please attach a note explaining the reason why you couldn’t renew on time.
- Fill out two copies of the application form. Click here to download the form.
- Present your existing Ethiopian Origin ID Card with two copies of it.
- Additional document showing Ethiopian Origin:
- Two copies of a Birth certificate which is authenticated through Ethiopian Ministry of Foreign AffairsAddis Abba; Attach Two copies of your old Ethiopian passport (blue or Burgundy Color). Please make sure to attach the pages which show your name, your picture, date of issue and expiration date of the passport; or
- Two copies of document authenticated by the Ministry of Foreign Affairs showing that you are the legal inheritor. The inheritor should be the son/daughter of biological parents who are/ was Ethiopians; or
- Two copies of the adoption court document. The document should be authenticated by the Ministry of Foreign Affairs. The adoption document must show that the adoptee was given to the adopter by Ethiopian parents and the adoptee even him/herself was an Ethiopian at the time of the adoption; or
- Two copies of the court document showing Ethiopian origin. The document should be authenticated by the Ministry of Foreign Affairs; or
- Two copies of the court document showing that one of the applicant’s parents or grandparents were Ethiopians. The document should be authenticated by the Ministry of Foreign Affairs Addis Ababa.
- Two copies of Valid Passport. The passport must be valid at least for more than 6 months.
- Five (5) recent, color passport size Photographs (with white background and the name of the applicant at the back of the photograph);
- If the Ethiopian Origin ID Card was issued through marriage, the couple should sign and submit a pledge form stating that their marriage is still valid (Click here to download the form) and should present two copies of valid Ethiopian Origin ID Card of the spouse.(temporarily suspended)
- A fingerprint of the Applicant (original and a copy). Please go to the nearest police station or to the companies authorized to take fingerprints. We prefer to have your fingerprint on their Fingerprint capture form. If not you can use ours (click here to download the form). Those who have already submitted a fingerprint upon receipt of an electronic Ethiopian Origin ID Card earlier are not required to submit again. However, if you have a yellow (manual) card, submitting a fingerprint is mandatory.
- Payment of $200 to daily euro rate in the form of money order payable to Embassy of Ethiopia Account.
- A self-addressed return Envelope with sufficient prepaid Postage(DHL TNT Bpost Express mail)
D. Replacing a Lost ID Card
A person who wishes to obtain a replacement of lost ID card should follow the steps outlined below.
- Fill out two copies of the application form. Click here to download the form.
- Two copies of a lost Ethiopian Origin ID Card (if applicable).
- An application letter stating the loss of Ethiopian ID card. Please state the Date and Place of Issue of the lost ID card on your letter.
- Additional document showing Ethiopian Origin:
- Two copies of a Birth certificate which is authenticated through Ethiopian Ministry of Foreign Affairs; or
- Attach Two copies of your old Ethiopian passport (blue or burgundy color). Please make sure to attach the pages which show your name, your picture, date of issue and expiration date of the passport; or
- Two copies of document authenticated by the Ministry of Foreign Affairs showing that you are the legal inheritor. The inheritor should be the son/daughter of biological parents who are/were Ethiopians; or
- Two copies of the adoption court document. The document should be authenticated by the Ministry of Foreign Affairs. The adoption document must show that the adoptee was given to the adopter by Ethiopian parents and the adoptee even him/herself was an Ethiopian at the time of the adoption; or
- Two copies of the court document showing Ethiopian origin. The document should be authenticated by the Ministry of Foreign Affairs Addis Ababa; or
- Two copies of the court document showing that one of the applicant’s parents or grandparents were Ethiopians. The document should be authenticated by the Ministry of Foreign Affairs.
- Two copies of a Valid Passport. The passport must be valid at least for 6 months.
- If the Ethiopian Origin ID Card was issued through marriage, the couple should sign and submit a pledge form stating that their marriage is still valid (Click here to download the form) and should present two copies of valid Ethiopian Origin ID Card of the spouse. ( temporarily suspended)
- A fingerprint of the Applicant (original and a copy) in person. if there is personal problem Please go to the nearest police station or to the companies authorized to take fingerprints. We prefer to have your fingerprint on their Fingerprint capture form. If not you can use ours (click here to download the form). Those who have already submitted a fingerprint upon receipt of an electronic Ethiopian Origin ID Card earlier are not required to submit again. However, if you have a yellow (manual) card, submitting a fingerprint is mandatory.
- Five (5) recent, colored photographs of size 3×4 cm with white background and name of the applicant at the back of the photograph.
- Payments should be made in the form of a Money Order payable to the Ethiopian Embassy Account in advance ;
- Replacement of a lost ID Card for the first time $240 to daily euro rate ;
- Replacement of a lost ID Card for the Second time $300 to daily euro rate ;
- Replacement of a lost ID Card for the third time and more $400 to daily euro rate ;
- A self-addressed return envelope which has a tracking number (DHL By post Express mail) with it.
E. Replacing a worn-out/Damaged ID Card
A person who wishes to obtain a replacement of Worn out / Damaged ID card should follow the steps outlined below.
- Fill out two copies of the application form. Click here to download the form.
- Two copies of Valid Passport. The passport must be valid at least for 6 months.
- Two copies of the worn-out/damaged Ethiopian Origin ID Card.
- A fingerprint of the Applicant (original and a copy). Please go to the nearest police station or to the companies authorized to take fingerprints. We prefer to have your fingerprint on their Fingerprint capture form. If not, you can use ours (click here to download the form)
- Five (5) recent, color passport size photographs (with white background and name of the applicant at the back of the photograph).
- Payment of $220 to daily euro rate in the form of Deposit Order payable to Ethiopian Embassy Account ;
- A self-addressed return envelope which has a tracking number (DHL TNT Bpost Express mail ) with it.