በብራሰልስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ በኔዘርላንድስ አምስተርዳም በመገኘት የቆንስላ አገልግሎት ሰጠ፣

በብራሰልስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ በኔዘርላንድስ አምስተርዳም በመገኘት የቆንስላ አገልግሎት ሰጠ፣
በብራሰልስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት ተደራሽነት ለማስፋት ኖቬምበር 29 ቀን 2025 ዓ.ም. በኔዘርላንድስ አምስተርዳም ከተማ በመገኘት ለአካባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ- ኢትዮጵያውያን ሰነዶችን የማረጋገጥ(Authentication/Legalization)፣ ውክልና (PoA) የመስጠት እና የመሻር፣ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የድጋፍ ደብዳቤዎች መስጠት፣ የትውልደ-ኢትዮጵያዊ መታወቂያ እና ፓስፖርት እድሳት፣ የልደት ሰርተፍኬት እና የዳያስፖራ ባንክ አካውንት መክፈት የቆንስላና የዳያስፖራ አገልግሎቶችን ሰጥቷል።
የዳያስፖራ ኮሚዩኒቲ አባላት አገልግሎቱን በቅርበት ማግኘት በመቻላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፤ መሰል ፕሮግራሞች በተደጋጋሚ እንዲዘጋጁ ጠይቀዋል።
ከአገልግሎቱ ጎን ለጎን ኤምባሲው ባደረገው ጥሪ መሰረት፣ ለአብርሆት ቤተ-መጽሀፍት የሚሆኑ የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መፅሃፍቶች በዳያስፖራው አባላት ተለግሰዋል። በተጨማሪም ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚውል የቦንድ ሽያጭ ተከናውኗል።