Legalization

እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒ አያይዘው ይላኩ፡፡

  • እንዲረጋገጥልዎ የፈለጉት የውክልና ሰነድ ሆኖ ኢትዮጵያዊ/ት ሆነው የአገልግሎት ዘመኑ ያላበቃ ፓስፖርት ወይም ያገልግሎት ዘመኑ ያላበቃ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ካለዎት የውክልና ሰነዱን ኖተራይዝ አስደርገው ከሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች ጋር በቀጥታ ወደ ኤምባሲው መላክ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን አገልግሎቱ የፀና የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ወይም አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከሌለዎት ውክልናውን በአማርኛና በእንግሊዘኛ ተጽፎ ኖተራይዝ በማድረግ በመጀመሪያ ባሉበት አገር ኦፊስ ቀጥሎ በምትገኙበት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተረጋገጠ በሁዋላ ወደ ኤምባሲያችን መላክ ይኖርብዎታል፡፡
  • ማንኛውም ለማረጋገጥ የሚቀርብ ዶክመንት ከቤኔሉክስ አገሮች የመነጩ (የተሰጠ) ከሆነ (ለምሳሌ – ያላገቡ መሆነዎትን የሚያረጋግጥ፣ የልደት የምስክር ወረቀት እና የመሳሰሉትን …) መጀመሪያ ካሉበት አካባቢ አገር ኦፊስ በመሄድ ዶኩመንቱን ካረጋገጡ በኋላ በምትገኙበት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተረጋገጠ በኋላ ወደ ኤምባሲያችን መላክ ይኖርበታል፡፡
  • ለማረጋገጥ የሚፈልጉት ዶኩመንት ከኢትዮጵያ የመነጨና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ከሆነ በቀጥታ ወደ ኤምባሲያችን በመላክ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ፣
  • ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number DHL TNT Bpost Express mail ባለው መሆን ይገባዋል፡፡ የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱም ሆነ የተዘጋጀለዎት ሰነድ ወደ እርሶ ተመላሽ ለመደረጉ ባለዎት የፖስታ Tracking Number በመጠቀም ማጣራት ሰለሚችሉ ይህንኑ መረጃ ለማረጋገጥ ወደ ኢምባሲው መደወል አይጠበቅብም፡፡

የክፍያ መረጃ (payment information)፡

ተ.ቁ የትምህረት፣ የልደት የጋብቻ፣ መንጃ ፈቃድና የመሣሠሉት

የምስክር ወረቀቶች  ( certificates of Educational, birth, Driving and other documents)

በዩሮ €
1 ኢትዮጵያውያኖች (For Ethiopians) 53.10
2 ለውጭ ዜጐች (For non Ethiopian)  81
ተ.ቁ የፍርድ ቤት ውሣኔዎችናቢዝነስ ፣ ሀብት ነክ ጉዳዮችየሚመለከቱ ሰነዶች ሙሉ ውክልና ( for Power of Attorney , cases  related court and property) በዩሮ €
1 ኢትዮጵያውያኖች (For Ethiopians) 55.80
2 ለውጭ ዜጐች (For non Ethiopian) 85.50

Please fill the forms carefully as described below and send them to us

  • If you are a holder of valid Ethiopian Passport or of valid Ethiopian Origin ID card, you can send the notarized document of Power of Attorney directly to the Embassy. If not, your Power of Attorney document should be authenticated by the Ministry of Foreign Affairs
  • All documents originating in the Benelux, such as Adoption, Trade Mark, Property Rights, Court Decisions, Birth Certificates, Marriage or Divorce Certificates, etc) must be authenticated by your Ministry of Foreign Affairs prior to applying at the Embassy.
  • All documents originating in Ethiopia should be authenticated by Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia.
  • All applications must be sent via e-mail with an envelop which has a TRACKING NUMBER. The applications must also have a self-addressed, prepaid (DHL TNT Bpost Express mail ) return envelop which has a tracking Number. You don’t have to call the Embassy to check whether your application has been received or returned back to you since you have the option to track it online at the respective mailing company’s website.

የተለያዩ ሰነዶችን ለማረጋገጥ

ሀ. ከቤኔሉክስ መንግስታት ለተሰጡ የተለያዩ ዶክመንቶችን ለማረጋገጥ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1 ሰነዱን መጀመሪያ ካሉበት አገር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አረጋግጦ ወደ ኤምባሲያችን መላክ ፣
2 የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ባንክ አካውንት ማስገባት /Deposit Order/ ሆኖ የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ ካያያዙ ሰነዱ የትምህርት፣የልደት፣ የጋብቻ፣ያላገባእና የሞት ሰርተፊኬት ከሆነ 53.10 ዩሮ ሲሆን በተመሳሳይ ከላይ የተጠቀሱት አገልግሎቶች ለማግኘት የሌላ አገር ዜጋ ከሆኑ ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ከሌለዎት ወይም አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከሌለዎት 81 ዬሮ ሲሆን ሰነዱ የፍርድ ቤት ከውርስ ፣ከሃብት ከንብረት ጋር የተያያዘ ከሆነ ለኢትዮጵያውያን 55.80 ዩሮ ለውጭ አገር ዜጎች 85.50 ዩሮ በባንክ አካውንት ገቢ ማድረግ፡፡
3 የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት (click here to download a form)
4 አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው DHLTNT Bpost Express mail ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣

ለ. በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ ከኢትዮጵያ ለመጡ የተለያዩ ሰነዶችን ለማረጋገጥ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1 መጀመሪያ ለማረጋገጥ የሚፈለገው ዶክመንት በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል
2 የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ በተፃፈ ባንክ ማስገባት / Diposit Order/ ሆኖ የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ ካያያዙ 53.10 ዩሮ ሲሆን የሌላ አገር ዜጋ ከሆኑ ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ከሌለዎት ወይም አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከሌለዎት 85.50 ዩሮክፍያ መፈፀም ነው፡፡
3 የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት (click here to download a form)
4 አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው DHL TNT Bpost Express mail ከነቴምብሩ አብሮ መላክ ይጠበቅቦታል ::

Documents such as Certificate of Education, Birth, Marriage, Driving Licence, etc

A. Authenticating Documents Originating in the Benelux States

  1. Notarized and authenticated documents by the State Office which issued the document; And then authentication of the same document by the Benelux of State.
  2. Copy of a Resident Card ( for Ethiopian passport holder);
  3. Holders of valid Ethiopian Passport or valid Ethiopian Origin ID Card are required to pay a Service fee of 53.10 euro per document in a money order. If not, a service fee of 81 euro per document in money order is required.
  4. A completed application form Click here to download.
  5. A self-addressed return envelope which has a tracking number (DHLTNT Bpost Express mail ) with it.

B. Authenticating Documents Originating in Ethiopia

  1. Prior to applying at the Embassy of Ethiopia for authentication of documents originating in Ethiopia, the documents have to be authenticated first by the Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia.
  2. Copy of a Resident Card ( for Ethiopian passport holder);
  3. Holders of valid Ethiopian Passport or valid Ethiopian Origin ID Card are required to pay a Service fee of 53.10 euro per document in a money order. If not, a service fee of 81 euro per document in Deposit order is required.
  4. A completed application form Click here to download.
  5. A self-addressed return envelope which has a tracking number (DHLTNT Bpost Express mail) with it.