የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በውጭ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ልዩ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ ከፈተ፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በውጭ ሃገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ልዩ አገልግሎት የሚሰጥ የመጀመሪያ ቅርንጫፉን በአዲስ አበባ ከፈተ፡፡
በቅርንጫፉ በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ትውልድ ሃገራቸው በመጡ ጊዜ የቁጠባ ሂሳቡን በመክፈት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ቅድሚያ ሰጥቶ የሚያስተናግድ ነው።
በአካል መቅረብ ለማይችሉትም በሚኖሩበት ሃገር አቅራቢያ በሚገኝ የኢትዮጵያ ኢምባሲ እና ቆንስላ ፅህፈት ቤት አማካኝነት የባንክ ሂሳቡን መክፈት ይችላሉ ተብሏል።
የቅርንጫፉ መከፈት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሃገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ሃገራዊ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን እንደሚያሳድግም ተጠቁሟል።
ከሶስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከሃገራቸው ውጭ እንደሚኖሩ ይገመታል።
EBC