በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት አማካኝነት በቤልጅዬም የአ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ ስልጠና እየተካሄደ ነው።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት አማካኝነት በጽ/ቤቱ ተግባርና ኃላፊነት፣ በጉዲፈቻ ህጻናት እቅድ አፈጻጸም እንዲሁም በአገራችን የህጻናት ድጋፍ ፕሮግራሞች ያተኮራ የሁለት ቀን ስልጠና ብራሰልስ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ መሰጠት ጀመረ።

ስልጠናው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት የተዘጋጅ ሲሆን፣ ከብራሰልስ፣ስቶኮልም፣ በርሊን እና ፍራንክፈርት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲዎችና ቆንስል ጄኔራል ለተውጣጡ ዲፕሎማቶች የስልጠናው ተሳታፊዎች ናቸው።