ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅርሱን ጠብቀው ላቆዩት ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና እንዲመለስ ትብብር ላደረገው የኔዘርላንድስ መንግስት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተረከቡትን የዘውድ ቅርስ በብሄራዊ ሙዚየም እንዲቀመጥ ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው አስረክበዋል፡፡
ዛሬ ማለዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ18ኛ ክፍለ ዘመን ዘውድ ለመመለስ ከመጡት የኔዘርላንድስ የውጪ ንግድ እና የልማት ትብብር ሚኒስትሯ ሲግሪድ ካግ ጋር ተገናኝተዋል።
ቅርሱ ከ1985 ዓ.ም. አንስቶ ጠፍቶ የቆየ ሲሆን፣ በጥቅምት 2011 ዓ.ም. በኔዘርላንዷ ሮተርዳም የተገኘ መሆኑ ተመልክቷል።
ከአራት መቶ ዓመታት በላይ እድሜ ያለው ይኸውን ቅርስ አቶ ሲራክ አስፋው የተባሉ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ድንገት እንዳገኙትና የተሰረቀ መሆኑን በማመን ለኢትዮጵያ መንግስት ለመመለስ አጋጣሚውን ሲጠብቁ እንደነበር ከዚህ በፊት መገለፁም ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሰረት ትውልደ ኢትዮጵያዊ አቶ ሲራክ ከኔዘርላንድስ መንግስት ተወካዮች ጋር በመሆን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የዘውድ ቅርሱን ለኢትዮጵያ መንግስት አስረክበዋል፡፡
በአስማማው አየነው