ክቡር ዶ/ር አክሊሉ ኃይለ ሚካኤል የሉግዘምበርግ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚን አነጋገሩ

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አክሊሉ ኃይለ ሚካኤል ዛሬ የካቲት 18 ቀን 2012 ዓም በኢትዮጵያ የሉግዘምበርግ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ የሆኑትን ሚስተር ዶሚኒክ ቼቮሎተን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ክቡር ዶ/ር አክሊሉ ኃይለ ሚካኤል በወቅቱ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ እና ሉግዘምበርግ ረጅም ዘመናት ያስቆጠረውን ግንኙነታቸውን በትምህርት፣ በኢኮኖሚ እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ ለማጠናከር የሚያስችሉ ሰፊ እድሎች እንዳለቸው ገልጸዋል። ክቡር ዶ/ር አክሊሉ በማያያዝም ኢትዮጵያ በተጠቀሱት ዘርፎች ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን ወደ ተግባር በመለወጥ የሁለቱን አገሮች ህዝቦች ፍለጎት ለማሟላት ትሰራለችም ብለዋል።

ሚስተር ዶሚኒክ ቼቮሎተን በበኩላቸው የሉዘምበርግ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት እና በኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ ያለውን ግንኘነት ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት ያለው መሆኑን በማስተወስ፤ ኤምባሲው ይህንን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።