ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 957 የላቦራቶሪ ምርመራ አንድ ሰው የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፁ።
ሚኒስትሯ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 123 መድረሱን በፌስቡክ ገፀቸው ላይ አስታውቀዋል።
ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ ከፑንትላንድ የተመለሰና በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ 30 ዓመት የጅግጅጋ ነዋሪ ነው።
በትናንትናው እለት 12 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውንም ነው ያመለከቱት።
ይህንንም ተከትሎ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 41 ደርሷል።