የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የሚሠጠውን እርዳታ “Suspend” ያደርጋል ብሎ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነት ቢሮ ያወጣውን ጽሁፍ “ዘግይቷል” በሚል ለውጦ በታህሳስ ወር 2013 ዓ.ም. እንደነበረው መልሶ አስተካክሎታል፤

 

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት Mr. Josep Borrell እ.ኤ.አ. በጃንዋሪ 15 ቀን 2021 ኢትዮጵያን አስመልክቶ በግላቸው Blog ባወጡት ጽሁፍ በትግራይ ክልል ገደብ የማይደረግበት የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ከሌለ ህብረቱ ለአገራችን የሚያደርገውን የበጀት ድጋፍ ‘Suspend’ እንደሚያደርግ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ በብራሰልስ የኢትዮጵያ ሚስዮን መሪ ክብርት አምበሳደር ሂሩት ዘመነ በአውሮፓ ኮሚሽኑ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ጋር በተከታታይ በመገናኘት ማብራርያ የጠየቁ ሲሆን፤ በMr. Borrell ጽሁፍ ላይ የበጀት ድጋፍ ‘Suspend’ ይደረጋል ተብሎ የወጣው ጽሁፉ ላይ ማስተካከያ ያደረገ መሆኑንና የቀጥተኛ በጀት ድጋፉን ከማዘግየት (postpone ከማድረግ) ባለፈ የአውሮፓ ህብረት የወሰደው ተጨማሪ እርምጃ እንደሌለ ለመረዳት ችለናል፡፡

ኤምባሲያችን ከኮሚሽኑ የስራ ኃላፊዎች ጋር በየጊዜው በመገናኘት የአውሮፓ ህብረት የበጀት ድጋፍ ለመልቀቅ ቅድመ-ሁኔታዎችን ባስቀመጠው መሰረት በተለይ በትግራይ ክልል እየተደረገ ያለውን የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቱን ለማሻሻል በመንግስት በኩል እየተደረገ ያለውን ጥረት በተከታታይ በማስረዳት ላይ ይገኛል፡፡