ክቡር አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን በኔዘርላንድ እና አካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ

ክቡር አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን በኔዘርላንድ እና አካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ
—————————————————————————–
በቤንሉክስ አገራት እና በአውሮፓ ህብረት ተቋማት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ክቡር እሸቴ ጥላሁን ወልደየስ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኔዘርላንድስ ንጉስ ግርማዊነታቸው Willem-Alexander Claus George Ferdinand ፌብሯሪ 19 ቀን 2025ዓ.ም. ዘ-ሄግ በሚገኘው Noordeinde ቤተ መንግስት አቅርበዋል።
የሹመት ደብዳቤያቸውን ማቅረባቸውን ተከትሎም በኔዘርላንድ እና አካባቢው ከሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን እና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ጋር በአገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በልማት እና የዳያስፖራው ተሳትፎ ጉዳዮች፣ ኤምባሲው በሚሰጣቸው አገልግሎቶች እና የኢትዮጵያ-ኔዘርላንድ ግንኙነት ጭብጦች ላይ ሠፊ ውይይት አድርገዋል። የትውውቅ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።
በወቅቱም ከተሳታፊ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ከልማት ተሳትፎ፣ ከአገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ እና ከአገልግሎት አሠጣጥ ጋር የተያያዘ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ቀርበው በክቡር አምባሳደር እሸቴና እና በዲፕሎማቶች ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ክቡር አምባሳደር በሚኖራቸው ቆይታ ከዳያስፖራው ጋር ተቀራርበው መስራት እንደሚፈልጉና ለሚፈልጉት አገልግሎትም ሆነ ውይይት ቢሮዎች ክፍት እንደሆኑ ገልፀዋል።
ዳያስፖራው ማህበረሰብ ለተካሄደው የትውውቅ ፕሮግራም እንዲሁም ለተሰጠው ማብራሪያ በማመስገን፤ ክቡር አምባሳደር በሚኖራቸው የስራ ቆይታ ተልዕኮዋቸውን በተሳካ ሁኔታ ለመወጣት በሚያደርጉት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚሰጡ እና ከኤምባሲው ጋር ተቀራርበው እንደሚሠሩ ገልፀዋል።