ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የልዑካን ቡድናቸው ዛሬ በሶማሊያ ሞቃዲሾ ጉብኝት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የልዑካን ቡድናቸው ዛሬ በሶማሊያ ሞቃዲሾ ጉብኝት አድርገዋል። ሁለቱ መሪዎች አስቀድሞ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ካደረጓቸው ውይይቶች የቀጠለ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል። ውይይታቸው በሰላም እና ፀጥታ፣ በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ እና በጋራ ሊሰሩ በሚችሉ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ላይ ያተኮረ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለትብብር እና የጋራ ጥቅም የቀጠናውን እምቅ አቅም አፅንዖት ሰጥተው እንደሚከተለው አንስተዋል።
“የአፍሪካ ቀንድ በሀብት የበለፀገ ነው። ለም ምድር፣ የተፈጥሮ ውሃ እና የሰው ኃይል ሀብቶች አሉት። ይሁንና ራሳችንን ለመመገብ ስንቸገር ይስተዋላል። ቀጠናዊ ትስስር የጋራ ህልማችንን እውን ለማድረግ እጅግ ጠቃሚ ነው።”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የልዑካን ቡድናቸውም ጉብኝቱን አጠናቀው ተመልስዋል።
Prime Minister Abiy Ahmed and his delegation held a visit to Mogadishu, Somalia, earlier today. The two leaders held extensive discussions, building on previous engagements to strengthen bilateral relations. Their talks focused on peace and security, the economy, diplomacy, and opportunities for joint infrastructure development.
Prime Minister Abiy Ahmed emphasized the region’s immense potential for cooperation and mutual benefit, stating:
“The Horn of Africa is rich in resources—fertile lands, fresh water, and human capital. Yet, as a region, we struggle to feed ourselves. This makes integration essential to achieving our shared aspirations.”
The Prime Minister and his delegation have concluded their visit and returned to Ethiopia.