አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና ለአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት አቀረቡ

አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና ለአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት አቀረቡ
————————————————–
በቤኔሉክስ አገራት እና በአውሮፓ ህብረት ተቋማት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር እሸቴ ጥላሁን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለክቡር የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አንቶኒዮ ኮስታ እና ለክብርት የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን ሜይ 20 ቀን 2025 ዓ.ም አቀረቡ።
በሥነ-ስርዓቱ ክቡር አምባሳደር እሸቴ ከሁለቱም የህብረቱ ፕሬዚዳንቶች ጋር አጭር ውይይት አድርገዋል። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ትብብር ያደገ ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ ያስቆጠረ ረጅም ግንኙነት አላቸው።