የብራሰልስ ሚሲዮን በኔዘርላንድስ ሮተርዳም ከተማ በመገኘት ለኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ አባላት የተለያዩ የቆንስላ አገልግሎቶችን ሰጠ፣
በብራሰልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለዜጎች የሚሰጠውን የአገልግሎት ተደራሽነት ከማስፋት አኳያ ጁን 7 ቀን 2025 ዓ.ም. በኔዘርላንድስ ሮተርዳም ከተማ በመገኘት በአካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተለያዩ የቆንስላ አገልግሎቶችን ሰጥቷል።
ወደ ሚሲዮን ለመምጣት በስራና የተለያዩ ምክንያቶች ላልቻሉ የኮሚዩኒቲ ማህበረሰብ በቅርበት አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉ አድናቆት ተችሮታል። ተመሳሳይ አገልግሎት እንዲቀጥልም የኮሚዩኒቲ አባላቱ ጠይቀዋል። ከቆንስላ አገልግሎት ጎን ለጎን በዕለቱ ከተገኙ የዳያስፖራ ማህበረሰብ ጋር በአገራዊ ልማትና ሰላም እንዲሁም የህዳሴ ግድብን በሚመለከት ውይይት ተደርጓል።
