በቤኔሉክስ አገራት ከሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ጋር የበይነ መረብ ወርሃዊ ውይይት ኖቬምበር 22 ቀን 2025 ዓ.ም. ተካሄደ፣
ውይይቱ በኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ፣ ታሪካዊ ዳራ እና በዳያስፖራው ሚና ላይ ያተኮረ ነበር። ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ፣ በታሪክ አጋጣሚ የተፈጠረውን ግዙፍ ጥፋት እና ስትራቴጂክ ስህተት ለማረም እና የሀገርን ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚደረግ ፍትሃዊ ትግል እንደሆነ ተሰምሮበታል። በዚሁ ሃሳብ በመስማማት አጀንዳውን በምልአት ለማራመድ መግባባት ላይ ተደርሷል። ዳያስፖራው ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ማግኘት እንድትችል በትጋትና በጋራ በመስራት በኩል ያለው ሚና የላቀ እንደሆነም የጋራ መግባባት ተደርሷል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳያስፖራ አካውንት ለመክፈት የተደረጉ አዳዲስ ማሻሻዮችን ላይ ገለፃ ተሰጥቷል። ውይይቱ ዳያስፖራው በብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ ያለውን ግንዛቤ እና ተሳትፎ የሚያሳድግ እንደሆነና በተከታታይ እንደሚካሄድ አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን አሳውቀዋል።




