የብራሰልስ ሚሲዮን በኔዘርላንድስ ሄግ ከተማ በመገኘት ለዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የተለያዩ የቆንስላ አገልግሎቶችን ሰጠ፣

የብራሰልስ ሚሲዮን በኔዘርላንድስ ሄግ ከተማ በመገኘት ለዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የተለያዩ የቆንስላ አገልግሎቶችን ሰጠ፣
በሚሲዩኑ ለዜጎች የሚሰጠውን የአገልግሎት ተደራሽነት ከማስፋት አኳያ ሜይ 23 ቀን 2026 ዓ.ም. በኔዘርላንድስ ሄግ ከተማ በመገኘት በአካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተለያዩ የቆንስላ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎቶችን ሰጥቷል።
በሥራና በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ብራሰልስ ሚሲዮን መምጣት ላልቻሉ የኮሚዩኒቲው አባላት አገልግሎቱን በቅርበት ማድረስ በመቻሉ ከፍተኛ አድናቆት የተቸረው ሲሆን፣ ማህበረሰቡም ተመሳሳይ አገልግሎቶች ወደፊትም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። ከቆንስላ አገልግሎቱ ጎን ለጎን፣ በዕለቱ ከተገኙ የዳያስፖራ አባላት ጋር በአገራዊ ልማት፣ ሰላም እና ኢንቨስትመንት ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ተካሂዷል።