በብራስልስ ቤልጄየም የአረንጓዴ አሸራ ፕሮግራም ተካሄደ

በብራስልስ ቤልጄየም የአረንጓዴ አሸራ ፕሮግራም ተካሄደ
በብራስልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት እና በክቡር አምባሳደር መኖሪያ ቤት የኢምባሲው ባልደረቦች የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሂደዋል::
በመርሃ ግብሩ ላይ በቤልጄም የኢትዮጵያ አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ባደረጉት ንግግር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር፣ ዓለምን እየገጠመው ላለው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ መቋቋም ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን ገልጸው፣ ከአፍሪካ ህብረት የአየር ንብረት ለውጥ መርኃ ግብር እና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታና የአፍሪካ አረንጓዴ ድልድይ ( African Union Climate Change and African Green Wall strategy ) የተዘመደ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህም ሌላ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብራችን የገጽ ምድር እና የከርሰ ምድር የውሃ ፍሰትን በመጨመር ድርቅን ለመከላከል እና የተፈጥሮ ሚዛንን ለመጠበቅ የሚያግዝ በመሆኑ፣ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በተለይ የዓባይ ውሃ የሚመለከታት ግብጽ የምታራምደው አቋም የተሳሳተና አመክንዮ የጎደለው መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ሃሳብ አፍላቂነት የተጀመረው የአረጓዴ አሻራ ፕሮግራም ህዝባችን ባህል አየሆነ እንደመጣ እና በሁሉም ኢትዮጵያዊ ደጅ እየደረሰ በመሆኑ የምንተክላቸው ችግኞች በዘላቂነት እንዲጸድቁና እንዲያድጉ በኃላፊነት ስሜት መንከባከብ፣ ሀገራችን ለያዘችው ግብ ስኬት የበኩላችንን ድርሻ መወጣት እንደሚገባ ክቡር አምባሳደሩ አሳስበዋል፡፡