26ኛው የግንቦት 20 የድል በዓል በብራሰልስ ቤልጄየም በኢፌዲሪ ኤምባሲ በድምቀት ተከበረ!
በኢፊዲሪ የብራሰልስ ኤምባሲ 26ኛው የግንቦት 20 የድል በዓል በቤኔሉክስ ሀገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓት ባህሪያት፣ የዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባታ ሂደትና ስኬቶች በሚል ረዕሰ በሀገራችን ባለፉት 26 ዓመታት ተግባራዊ እየሆነ የሚገኘው ህገ-መንግስታዊ ስርዓት እና የተገኙ ስኬቶች በሚል በቀረበ የመወያያ ፅሁፍ ከዲያስፖራ አባላቱ ጋር የፓናል ውይይት በማካሄድ በዓሉ በድምቀት ተከብሯል፡፡
በበዓሉ ክቡር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በቤኔሉክስ እና ቦልቲክስ ሀገራት እንዲሁም በአውሮፓ ህብረት ተቋማት የኢፊዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር በፓናል ውይይቱ ባቀረቡት ጽሁፍ እንዳሉት በሀገራችን ተግባራዊ እየሆነ ያለው የፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በአህዳዊ ስርዓት አስተዳደር፣ በከፋ ድህነትና የዲሞክራሲ እጦት ውስጥ ከነበረች ሀገር እንዲሁም የሰላምና ፀጥታ ችግር በበዛበት የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ውስጥ ሆኖ በርካታ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ስኬቶችን በማስመዝገብ ላይ የሚገኝ በህገ-መንግስት የሚመራ ሰርዓት ነው ብለዋል፡፡
አያይዘውም የሀገራችንን የህገ-መንግስት ታሪካ ወደ ኋላ በማስተዋስ የንጉሱ ስርዓት ህገ-መንግስት ከንጉሱ ለህዝቡ የተሰጠና ስልጣን በዘር-ሀገርና መለኮታዊ ነው የሚገኝ ነው ብሎ የሚደነግግ እንዲሁም የአምባገነኑ የደርግ ስርዓት የነበረው ደግሞ ፀረ-ዲሞክራሲያዊ በመሆኑ ህዝቦችን ለጭቆና በመዳረጉ ሀገራችን ለከፍ ድህነትና ኋላ ቀርነት እንዲሁም ለተራዘመ የእርስ በርስ ጦርነት ተጋልጣ እንደነበር አብራርተዋል፡፡ በሀገራችን የመሬት፣ የብሔር እንዲሁም ጠንካር የአህዳዊ መንግስት እና የመልማት መብትን መንፈግ ጋር ተያይዞ የነበረውን ጭቆና በመቃወም በበርካታ የሀገራችን አካባቢዎች የተቀሰቀሰው የገበሪዎች፣ የተማሪዎች እንዲሁም የታክሲ ሹፌሮች ተቃውሞ እና አመፅ እንዲሁም የትጥቅ ትግሉ ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡
ስለሆነም በተካሄደው መራራ የትጥቅ ትግል ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. በድል የተቋጨ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወያይተው ያፀደቁትና የጋራ ቃል-ኪዳናቸው የሆነው ህገ-መንግስታዊ ፌደራላዊ ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ በርካታ ለውጦችን በማስመዝገብ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢፊዲሪ ህገ-መንግስት ዲሞክራሲያዊ ባህሪያት ያሉት ሲሆን፣ ህዝቡ በአካባቢያዊ ጉዳዮች በተለያዩ ምክር ቤቶች በቀጥታ እንዲሁም በሀገራዊ ጉዳዮች ራሱ በወከላቸው የስልጣን ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን፣ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ራስን በራስ በማስተዳደር እስከ መገንጠል መብት ተጠቃሚ በመሆናቸው ከአሁን በፊት የመገንጠል ጥያቄ ያነሱ የነበሩ ጠባብ ሀይሎችም በአሁኑ ወቅት የመገንጠል ጥያቄ ለማንሳት የሚያስችል ምንም ሁኔታ ባለመኖሩ ህብረ-ብሔራዊነቱ የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንዲሁም የፖለቲካ ጥቅሞችን ማረጋገጥ የቻለ ነው ብለዋል፡፡ ህገ-መንግስቱ የግልና የቡድን መብቶችን ያከበረ ሲሆን፣ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የመሬት ባለቤት ያደረገና የአናሳ ማህበረሰቦችንም መብትና አያያዝ እንዲሁም የፖለቲካ ተሳትፎ ያስከበረ ነው ብለዋል፡፡ ክቡር አምባሳደሩ በገለፃቸው እንዳሉት ህገ-መንግስቱ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ፣ዋስትና ያለው ዲሞክራሲ ማስፈን እንዲሁም ፍጣን ልማት በማረጋገጥ አንድ የጋራ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማህበረሰብን መገንባት ዓላማዎቹ አድርጎ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ዚጎች በህገ-መንግስቱ ዓላዎችና ይዘቱ ላይ የጋራ መግባባትን በማሳደግ የልማታዊነት አስተሳሰብ በመጎናጸፍና ኪራይ ሰብሳቢነትን በመዋጋት የሀገራችንን የህዳሴ ጉዞ ማፋጠን እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡ ህገ-መንግስቱ ዋና ዋና መርሆዎች ያሉት ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ህዝቦች የሉዓላዊ የስልጣን ባለቤቶች ሲሆኑ፣ የህገ-መንግስት የህጎት ሁሉ የበላይ ህግ መሆኑን እንዲሁም፣ የሰበአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር፣ የመንግሰትና ሀይማኖት የተለያዩ መሆናቸውና የመንግስት ተጠያቂነትና ግልጽነትን ናቸው፡፡ ስለሆነም ዲያስፖራው በህገ-መንግሰቱ ላይ ለውን ግንዛቤ በማሳደግ በሀገር ግንባታ ሂደቱ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ክቡር አምባሳድ ተሾመ ቶጋ እንዳሉት የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓት ሀገሪቱን ከብተና የታደገና ባለፉት ሀያ ስድስት ዓመታት በለውጥ ጎዳና እንድትራመድ ማድረግ የቻለ ሲሆን፣ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በጋራና በራስ አስተዳደር የዲሞክራሲ መርሆዎችን ያረጋገጠ እንዲሁም፣ ሀገራችን ዓለም ባረጋገጠው መልኩ በዓለም ፈጣን የኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገት በማስመዝገብ ተርታ እንድትሰለፍ ያደረጋት ስርዓት መገንባት ተችሏል ብለዋል፡፡
በዚህም ውስጥ ሀገራችን ለሁለት አስርት ዓመታት ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት ስመዘገበች ሲሆን፣የዜጎች የነፈስ ወከፍ ገቢ በ2002 ከነበረበት 373 ዶላር በ2008 ወደ 794 የአሜሪካን ዶላር ከፍ ብሏል፡፡ ሀገራችን በመሰረተ ልማት መስክ በተለይም በመንገድ ፣ በኢሌክትሪክ ሀይል ልማት እና በባቡር ልማትና በኤርፖርቶች ድርጅት ግንባታ ተጨባጭ የልማት ውጤቶች ተገኘተዋል ብለዋል፡፡ በማህበራዊ ልማት መስክ ሀገራችን በጤናው መስክ በተከተለችው ውጤታማ ፖሊሲ 100 ፐርሰንት የጤና ሽፋን በማድረስ፣ በመስኩ ዋና ዋና የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች ያሳካች ሲሆን፣ በትምህርት መስክ እንዲሁም የአንደኛ ደረጃ የትምህርት ሽፋን 100 ፐርሰንት በማሳካት በሁለተኛ ደረጃ እንዲሁ 41 በመቶ ያደገ ሲሆን፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ 35 በማሳደግ በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ተመራቂ ተማሪዎችን በየዓመቱ በማሰልጠን የኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገቱን በማሳለጥ ላይ ትገኛለች፡፡
የዲያስፖራ አባላት በበኩላቸው ለተሰጣቸው ገለፃ በማመስገን በሀገራችን የህግ የበላይነት እንዲከበር በውጭም ይሁን ውስጥም ለሚገኙ የሀገሪቱ ዜጎች ስለ መብትና ግዴታ እንዲሁም ስለ ፌደራላዊ ስርዓቱ፣ ስለ ህገ-መንግስቱ አጠቃላይ ባህሪት፣ መርሆዎች እንዲሁም እሴቶች ትምህርትና ስልጠና ሊሰጥ ይገባል፡፡ በሀገሪቱ የተጀመረው ልማትና የህዳሴ ጉዞ በአደናቃፊ ሀይሎች እንዳይሰናከል መንግስት በተለይ መሪ ድርጅቱ ኢህአዴግ አበክሮ ሊሰራ ይገባል፡፡ አያይዘውም በሀገሪቱ በህገ-አውጭው፣ በህግ-ተርጓሚው እና በህገ- አስፈፃሚው መካከል ያለው የተጠያቂነትና ግልፅነት እንዲሁም የስልጣን ቁጥጥር መርህ መሰረት ባደረገ መልኩ ሊከናወን ይገባል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ለተነሱ ጥቄዎችና አስተያየቶች ምለሽ በመስጠት በቤኔሉከስ ሀገራት ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሀገራችን በተጀመረው የፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እንዲሁም እየተመዘገበ በሚገኘው ኢኪኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ በማስተላላፍ በዓሉ ፍፃሜ አግኝቷል፡፡ ስለሆነም በዕለቱ የተካሄደውን በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀውን ሪፖርት የላክን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የኢፌዲሪ ኤምባሲ
ብራሰልስ