36ኛዉ የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ ጎን ለጎን የኢጋድ ዉጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ እና በሠላም ስምምነት አፈጻጸም ዙሪያ ጥር 30 ቀን 2012 መክሯል ።
የወቅቱ የኢጋድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ም/ቤት የሆኑት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስማ አብደላ በኢጋድ የደቡብ ሱዳን ልዩ ልዑክ ኢስማኤል ዋይስ ሪፓርት እንዲሰማ አድርገዋል ። ሪፓርቱ የደቡብ ሱዳን አጠቃላይ የፓለቲካ የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ሁኔታ እየተሻሻለ በመምጣቱ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፃል። በሌላ በኩል ለደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግሰት ምስረታ ወቅት ሁለት ጊዜ እንዲሸጋገር ምክንያት የሆኑት አሳሳቢ ጉዳዮች አሁንም አለመፈታታቸው መሠረታዊ ችግር መሆኑ ተነስቷል ። በተለይም የውሁድ ሠራዊት ምስረታ ሂደት መጓተት እንዲሁም የክልሎች ብዛትና የድንበር አከላለል ጉዳዮች አለመቋጨት እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ በመሆኑ ኢጋድ ግልፅ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንዳለበት ታምኗል። ቀነገደቡ ተከብሮ በቀሩት ጥቂት ቀናት ከስምምነት እንዲደረስ ጥሪ ቀርቧል።