የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ቀን በብራሰልስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ በድምቀት ተከበረ

የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ቀን በብራሰልስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ በድምቀት ተከበረ
የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ቀን በብራሰልስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ ዲፕሎማቶች፣ ቤተሰቦቻቸው እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ዛሬ ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. በድምቀት ተከብሯል።
እለቱን በማስመልከት ክቡር አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን የስነ መንግስት አሰራር እና የዘመናት ዲፕሎማሲ ታሪክ ባለቤት መሆኗን አንስተው፣ የዲፕሎማሲ ቀን መከበሩ የተገኙ ውጤቶችን ለመዘከርና ለወደፊቱ የደመቁ አዳዲስ ድሎችን በአግባቡ ለመዘከር አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።
በመርሃ- ግብሩ በዲፕሎማሲ ዓለም ሰፊ ልምድ ያካበቱ ዲፕሎማቶች የስራ እና የህይወት ልምድ ልውውጥ እንዲሁም በብራሰልስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ ያገለገሉ የቀድሞ አምባሳደሮችን የሚያስተዋውቅ ዝክር ቀርቧል። በቤኔሉክስ አገራትና አውሮፓ ህብረት በመሪ ደረጃ የተደረጉ ጉብኝቶችን የሚያሳይ ቪዲዮም ታዳሚዎች እንዲመለከቱ ተደርጓል።
በዲፕሎማሲው ዘርፍ ረጅም ዘመንና የላቀ አገልግሎት ላበረከቱት ክብርት አምባሳደር ፎርቱና ዲባኮ የእውቅና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
የኬክ ቆረሳና የቤተሰብ ፎቶግራፍ ፕሮግራም እንዲሁም ከዳያስፖራ አባላት ጋር ለመቋደስ የተዘጋጀው መስተንግዶ የበዓሉን ድምቀት ጨምሮታል።