ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ኔዘርላንድስ ድጋፏን ትቀጥላለች

ኢትዮጵያ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ መር ለምታደርገው ኢኮኖሚያዊ ሽግግር የኔዘርላንድስ ሕዝብና መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ በኢትዮጵያ የአገሪቱ አምባሳደር ገለጹ።

አምባሳደር ሊዲ ረሜልዝዋል ኢትዮጵያ ለምታደረገው መዋቅራዊ ሽግግር አገራቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል።

በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ80 በላይ የኔዘርላንድስ ኩባንያዎች በግብርና ኢንቨስትመንት መሰማራተቸውን ጠቅሰው ኩባንያዎቹ አገሪቱ ለምታደርገው የኢንዱስትሪ ሽግግር ጠቃሚ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በቀጣይ ሦስት ዓመታት ለምታከናውናቸው የልማት ሥራዎች ማስፈጸሚያ የሚውል 2 መቶ 18 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ሐገራቸው እንደምሰጥ አምባሳደሩ አመልክተዋል።

ኔዘርላንድስ ከፍተኛ የውኃ ኃብት ባለቤት አገር እንደሆነች ያስታወሱት አምባሳደሯ የውኃ ኃብትን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ያላትን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማጋራት እየሰራች እንደምትገኝ አስታውቀዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው።