አየርላንድ ለኢትዮጵያ 200 ሺህ ዩሮ እርዳታ ሰጠች

የአየርላንድ መንግስት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የህግ ድጋፍ አገልግሎት የሚውል 200 ሺህ ዩሮ በእርዳታ ሰጠ።

የእርዳታ ስምምነቱን የተፈራረሙት በኢትዮጵያ የአየርላንድ አምባሳደር ኤደን ኦሆራና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ናቸው።

አምባሳደር ኦሆራ እንዳሉት ኢትዮጵያ በሰብአዊ መብት ዙሪያ እያከናወነች ላለው ጠንካራ እንቅስቃሴ አገራቸው የምታደርገውን ሁለንተናዊ እገዛ አጠናክራ ትቀጥላለች።

በአገሪቱ ውስጥ በተመረጡ 8 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች እየተሰጠ ያለው የህግ ድጋፍ አገልግሎት እንዳስደሰታቸውና በቀጣይም የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አምባሳደር ኦሆራ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አምባሳደር ጥሩነህ ዜና በበኩላቸው ኮሚሽኑ እያከናወናቸው ካሉ ፕሮጀክቶች መካከል ነፃ የህግ ማማከርና ጥብቅና አገልግሎት አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

ኮሚሽኑ ለሚያከናውናቸው ተግባራት የተለያዩ አገራት ድጋፍና እርዳታ እያደረጉ መሆኑንና የአየርላንድ መንግስትም በሌሎች ፕሮግራሞች ላይ ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ ለህግ ድጋፍ አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋፆ እያበረከተ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱን እየሰጡ ያሉት ዩኒቨርስቲዎች መቐለ፣ አክሱም፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ወላይታ ሶዶ፣ ዲላ፣ አዳማና ጂማ ዩኒቨርስቲ ናቸው።

ችግሩ ለመቅረፍም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ሴት ጠበቆች ማህበር እንዲሁም ከዩኒቨርስቲዎች ጋር በመተባበር በመላ ሃገሪቱ 130 የሚሆኑ ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ተከፍተዋል፡፡

ባለፉትሶስትአመታትብቻከ20 ሺህበላይዜጎችየአገልግሎቱተጠቃሚመሆናቸውንና በቀጣይምወደ 500 የሚደርሱማእከላትንየመክፈትእቅድመያዙን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል፡፡