ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ብራስልስ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በድምቀት ተከበረ!

ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ብራስልስ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በድምቀት ተከበረ!
በቤልጂየም ብራስልስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል 19ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በድምቀት አክብሯል።
በበዓሉ አከባበር ወቅት የኤምባሲው ባልደረቦች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ፊት በመቆም ለአገራቸውና ለሰንደቅ ዓላማቸው ያላቸውን ፍቅርና ክብር የገለጹ ሲሆን፣ የሀገራቸውን አንድነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ለሚከፈለው መስዋዕትነት አክብሮትና በበኩላቸው የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመፈፀም ያላቸውን ቁርጠኝነት አድሰዋል።
የሚሲዮኑ መሪ ክቡር አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ከብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጋር የተያያዙ የአብሮነትንና የብሔራዊ መግባባት መልእከቶችን አስተላልፈዋል። “የከሸፉ ፖለቲከኞች በሚያራምዱት አጥፊ አቋም የኢትዮጵያን ህዝብ የሰንደቅ ዓላማ ክብር ከህዝብ ልብ ለማውጣት እንደማይችሉ ታላቁ የትግራይ ህዝብ አስመስክሯል” ብለዋል። በዚህ ረገድ ፓለቲከኞች ለከት ያለውና ከእለት እንጀራቸው ያለፈ አቋም መያዝ እንዳለባቸው አመልክተዋል። በመቀጠል የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በመዘመር ሰንደቅ ዓላማ የመስቀል መርሃ-ግብር ተካሂዶ የእለቱ ዝግጅት ተጠናቅቋል።