ክቡር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣ በቤልጂየምና በኔዘርላንድስ ከሚኖሩ የኮሚኒቲ አመራረች ጋር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፣

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በብራስልስና በአካባቢው ከሚኖሩ የዳያስፖራ አመራሮችና የአውሮፓ ዲፌንድ ኢትዮጵያ አስተባባሪዎች ጋር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ አራት አባላት ያሉትን የልዑካን ቡድን በመምራት ለሥራ ጉዳይ በአሁኑ ወቅት በብራስልስ የሚገኙ ሲሆን፣ ዓርብ ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. በብራስልስና በአካባቢው ከሚኑሩ የዳያስፖራ አመራሮችና አስተባባሪዎች ጋር በአካል፣ እንዲሁም በኔዘርላንድስ ከሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት እና በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ከሚገኙ የዲፌንድ ኢትዮጵያ አስተባባሪዎች ጋር በዙም ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ በውይይቱ መግቢያ ላይ ባለፉት ሦስት ዓመታት በተለያዩ አገሮች በሚኖረው የዳያስፐራ ማኅበረሰብ የተደረጉ እንቅስቃሴዎችንና ድጋፎችን በተለይም በኮቪድ 19 መከላከል፣ ለመከላከያ ሠራዊታችንና በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተከሰተው ግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የተደረገውን የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ፣ እንዲሁም በ#NoMore እንቅስቃሴ፣ በታላቁ ጉዞ ወደ አገርቤትና በዒድ እሰከ ዒድ መርሃ-ግብር የተደረጉ የአድቮኬሲና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎችን በመዘርዘር በራሳቸውና በመንግሥት ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በማስከተልም በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሰብሳቢዎቹ እንዲነሱ በጋበዙት መሠረት በአገራችን የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እየተደረገ ስላለው እንቅስቃሴና በዚሁ ሂደት የዜጎችን መብት ስለማስከበር፣ በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የሚገኙ ሰዎች አያያዝን በተመለከተ በአቃቤ ሕግና እና በፖሊስ መካከል ሚዛናዊ መስተጋብር ስለማስፈን፣ የተዛባ የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀምን ፈር ለማስያዝ ምን እየተደረገ እንደሆነ፣ በፍትህ ዘርፍ የሚካሄደው የሪፎርም ፕሮግራም በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና ሌሎችም በርካታ ጥያቄወዎችን አንስተዋል፡፡ ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ክቡር ሚኒስትሩ ሠፊ ጊዜ በመውሰድ ጥልቅ ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ክቡር ሚኒስትሩ በዳያስፖራ ማኅበረሰቡ እየተደረገውን የአድቮኬሲና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ሥራ አድንቀው ይኸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል::

Read more

H.E. Gedion Timothewos, Minister for Justice of FDRE confers with Members of European Parliament

H.E. Gedion Timothewos, Minister of Justice of the FDRE, during his working visit in Brussels from 15 to 18 June, met and discussed with various officials of the EU institutions. In his further engagement with the EU parliamentarians, he met Honorable Maria Arena, Chair of the Sub-Committee for Human rights, Honorable Urmas Paet, Vice-Chair for the Foreign Affairs Committee and Honorable Javier Nart, member of the European Parliament Foreign Affairs Committee.

Read more

The 114th Council of Ministers of the OACPS concludes its meeting

The 114th Council of Ministers of the Organization of the African, Caribbean and Pacific States (OACPS), which was held on the 8th and 9th June 2022 in Brussels, Belgium, concluded its meeting. The delegation of Ethiopia led by H.E. Ms. Semereta Sewasew, State Minister of Finance of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, took part in the Council sessions. Read more